ኢዩ ተነሥቶ እንደገና ጉዞ ቀጠለ፤ በመንገድ ሳለም የሬካብን ልጅ ኢዮናዳብን አገኘ፤ ኢዩም ሰላምታ ከሰጠው በኋላ “እኔና አንተ በሐሳብ አንድ ነን፤ ታዲያ ከእኔ ጋር ትተባበራለህን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮናዳብም “አዎ እተባበርሃለሁ” ሲል መለሰ። ኢዩም “እንግዲያውስ ጨብጠኝ” ሲል መለሰለት፤ እጅ ለእጅ ተያይዘው ኢዩ ደግፎት በሠረገላው ላይ አስቀመጠውና፥
ገላትያ 2:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተሰጠኝን ጸጋ አውቀው፥ ምሰሶዎች መስለው የሚታዩ ያዕቆብ፥ ኬፋና ዮሐንስ፥ እነርሱ ወደ ተገረዙት እኛ ወደ አሕዛብ እንድንሄድ ለእኔና ለበርናባስ የኅብረት ቀኝ እጃቸውን ሰጡን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ አዕማድ የሚቈጠሩት ያዕቆብ፣ ኬፋና ዮሐንስም የተሰጠኝን ጸጋ ባስተዋሉ ጊዜ፣ ለእኔና ለበርናባስ የትብብር ቀኝ እጃቸውን ሰጡን፤ ከዚያም እኛ ወደ አሕዛብ፣ እነርሱ ደግሞ ወደ አይሁድ እንድንሄድ ተስማሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ምሰሶ መስለው የሚታዩት መሪዎች ያዕቆብና ጴጥሮስ ዮሐንስም እግዚአብሔር በጸጋ ይህን ልዩ የአገልግሎት ዕድል እንደ ሰጠኝ በተረዱ ጊዜ ለእኔና ለበርናባስ የመተባበራቸው ምልክት የሆነውን ቀኝ እጃቸውን ሰጡን፤ እኛ ወደ አሕዛብ እንድንሄድ እነርሱም ወደ አይሁድ እንዲሄዱ ተስማሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰጠኝንም ጸጋ ዐውቀው አዕማድ የሚሏቸው ያዕቆብና ኬፋ፥ ዮሐንስም እኛ ወደ አሕዛብ፥ እነርሱም ወደ አይሁድ እንድንሄድ ለእኔና ለበርናባስ ቀኝ እጃቸውን ሰጡን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ የተሰጠኝን ጸጋ አውቀው፥ አዕማድ መስለው የሚታዩ ያዕቆብና ኬፋ ዮሐንስም እኛ ወደ አሕዛብ እነርሱም ወደ ተገረዙት ይሄዱ ዘንድ ለእኔና ለበርናባስ ቀኝ እጃቸውን ሰጡን፤ |
ኢዩ ተነሥቶ እንደገና ጉዞ ቀጠለ፤ በመንገድ ሳለም የሬካብን ልጅ ኢዮናዳብን አገኘ፤ ኢዩም ሰላምታ ከሰጠው በኋላ “እኔና አንተ በሐሳብ አንድ ነን፤ ታዲያ ከእኔ ጋር ትተባበራለህን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮናዳብም “አዎ እተባበርሃለሁ” ሲል መለሰ። ኢዩም “እንግዲያውስ ጨብጠኝ” ሲል መለሰለት፤ እጅ ለእጅ ተያይዘው ኢዩ ደግፎት በሠረገላው ላይ አስቀመጠውና፥
ወደ ኢየሱስም አመጣው። ኢየሱስም ተመልክቶ “አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህ፤ አንተ ኬፋ ትባላለህ” አለው፤ ትርጓሜውም “ጴጥሮስ” ማለት ነው።
ግን ዝም እንዲሉ በእጁ ጠቅሶ ጌታ ከወኅኒ እንዴት እንዳወጣው ተረከላቸውና “ይህን ለያዕቆብና ለወንድሞቹ ንገሩ፤” አላቸው። ወጥቶም ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።
ከብዙ ክርክርም በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው “ወንድሞች ሆይ! አሕዛብ ከአፌ የወንጌልን ቃል ሰምተው ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር በመጀመሪያው ዘመን ከእናንተ እኔን እንደ መረጠኝ እናንተ ታውቃላችሁ።
እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችሁ እንደሰጣችሁ እምነት መጠን፥ በረጋ አእምሮ አስቡ እንጂ ማሰብ ከሚገባችሁ በላይ ራሳችሁን ከፍ አድርጋችሁ እንዳታስቡ በተሰጠኝ ጸጋ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ እናገራለሁና።
ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ አሁን የሆንሁትን ሆኛለሁ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋ ከንቱ አልሆነም፤ ይልቁን ከሁሉም በላይ በትጋት ሠርቻለሁ፤ ሆኖም ግን እኔ ሳልሆን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው።
በመመካቴ ሞኝ ሆኜአለሁ! ይህ እናንተ ግድ ስላላችሁኝ የሆነ ነው። እኔ ከምንም የማልቆጠር ብሆን እንኳን፥ ከዋነኞቹ ሐዋርያት በምንም አላንስምና፥ በእርግጥም እናንተ ስለ እኔ መናገር ይገባችሁ ነበር።
እንደ ተገለጠልኝም ወጣሁ፤ ምናልባትም በከንቱ እንዳልሮጥ ወይም ሮጬ እንዳልሆን፥ በአሕዛብ መካከል የምሰብከውን ወንጌል፥ በመሪነታቸው ለታወቁት ለብቻቸው አስታወቅኋቸው።
ይህ ሳይሆን ቀርቶ ብዘገይ ግን፥ በዚህ በጻፍሁልህ ትእዛዝ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ የእውነት ዓምድና መሠረት በሆነችው በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ እንድታውቅ ነው።
እናንተም ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን እንነግራችኋለን። ኅብረታችንም ከአብና ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።
ድል የሚነሣውን በአምላኬ ቤተ መቅደስ ዓምድ አደርገዋለሁ፤ ወደፊትም ከዚያ ከቶ አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም፥ ማለትም ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደውን የአዲሲቱን ኢየሩሳሌምን ስም፥ እንዲሁም አዲሱን ስሜን በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።