እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “ለራስህ ረጅም ዕድሜ ወይም ሀብት ለማግኘት ወይም ጠላቶችህ እንዲጠፉልህ መመኘት ሳይሆን በትክክለኛ ፍርድ ማስተዳደር የምትችልበትን ጥበብ ስለ ጠየቅህ፥
ዕዝራ 8:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ አለቆቹም ወደ ኤሊዔዘር፥ አሪኤል፥ ሽማዕያ፥ ኤልናታን፥ ያሪብ፥ ኤልናታን፥ ናታን፥ ዘካርያስ፥ ሜሹላምና እንዲሁም ወደ መምህራኑ ወደ ዮያሪብና ኤልናታን ላክሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ መራሕያኑን አልዓዛርን፣ አርኤልን፣ ሸማያን፣ ኤልናታንን፣ ያሪብን፣ ኤልናታን፣ ናታንን፣ ዘካርያስንና ሜሱላምን እንዲሁም መምህራኑን ዮያሪብንና ኤልናታንን አስጠራኋቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ኤሊዔዘር፥ አሪኤል፥ ሸማዕያ፥ ኤልናታን፥ ያሪብ፥ ኤልናታን፥ ናታን፥ ዘካርያስና መሹላም ተብለው ወደሚጠሩ ዘጠኝ መሪዎች፥ እንዲሁም ዮያሪብና ኤልናታን ተብለው ወደሚጠሩ ሁለት መምህራን ላክሁባቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ አለቆቹም ወደ አልዓዛር፥ ወደ አርኤል፥ ወደ ሰማአያ፥ ወደ ሀሎናም፥ ወደ ያሪብ፥ ወደ ሄልናታን፥ ወደ ናታን፥ ወደ ዘካርያስ፥ ወደ ሜሱላም፥ ደግሞም ወደ ዐዋቂዎቹ ወደ ዮያሪብና ወደ ሄልናታን ላክሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ አለቆቹም ወደ አልዓዛር፥ ወደ አርኤል፥ ወደ ሸማያ፥ ወደ ኤልናታን፥ ወደ ያሪብ፥ ወደ ኤልናታን፥ ወደ ናታን፥ ወደ ዘካርያስ፥ ወደ ሜሱላም፥ ደግሞም ወደ አዋቂዎቹ ወደ ዮያሪብና ወደ ኤልናታን ላክሁ። |
እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “ለራስህ ረጅም ዕድሜ ወይም ሀብት ለማግኘት ወይም ጠላቶችህ እንዲጠፉልህ መመኘት ሳይሆን በትክክለኛ ፍርድ ማስተዳደር የምትችልበትን ጥበብ ስለ ጠየቅህ፥
እስራኤልም የሚገባውን እንዲፈጽም የዘመኑን ሁኔታ የሚያውቁ ጥበበኞች ሰዎች የይሳኮር ልጆች አለቆች ሁለት መቶ ነበሩ፤ ወንድሞቻቸውም ሁሉ ይታዘዙአቸው ነበር።
እንዲሁም ኪራም እንዲህ አለ፦ “ሰማይንና ምድርን የፈጠረ፥ ለጌታም ቤተ መቅደስ ለመንግሥቱም ቤተ መንግሥት እንዲሠራ ጥበበኛና ብልሃተኛ አስተዋይም ልጅ ለንጉሡ ለዳዊት የሰጠ የእስራኤል አምላክ ጌታ ቡሩክ ይሁን።
በካሲፍያ ስፍራ አለቃ ወደ ሆነው ወደ ኢዶ ላክኋቸው፥ ለአምላካችን ቤት አገልጋዮችን እንዲያመጡልን በካሲፍያ ስፍራ ለሚኖሩት ለኢዶና ለወንድሞቹ ለቤተ መቅደስ አገልጋዮች ምን የሚነግሩአቸውን አስታወቅኳቸው።
የአምላካችን መልካም እጅ በላያችን ላይ ስለ ነበረች፥ የእስራኤል ልጅ የሌዊ ልጅ ከሆነው ከማሕሊ ልጆች ወገን የነበረውን አስተዋይ ሰው ሼሬብያን፥ ከእርሱም ጋር ዐሥራ ስምንት ልጆቹንና ወንድሞቹን አመጡልን።
የእግዚአብሔር ልጅ እንደመጣ፥ እውነት የሆነውን እንድናውቅ ማስተዋልን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነት በሆነው በእርሱ እንኖራለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው።