La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዕዝራ 4:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዘሩባቤል፥ ኢያሱና የቀሩትም የእስራኤል አባቶች አለቆች፦ “የአምላካችንን ቤት ማነፅ ለእኛና ለእናንተ አይደለም፥ እኛ ለብቻችን ሆነን ንጉሥ ቂሮስ የፋርስ ንጉሥ እንዳዘዘን ለጌታ ለእስራኤል አምላክ ቤት እንገነባለን” አሉአቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዘሩባቤል፣ ኢያሱና ሌሎቹ የእስራኤል ቤተ ሰቦች አለቆች ግን፣ “ለአምላካችን ቤተ መቅደስ እንድትሠሩ ከእኛ ጋራ የሚያገናኛችሁ ምንም ነገር የለም። የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ ባዘዘን መሠረት ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የምንሠራው እኛ ብቻ ነን” ሲሉ መለሱላቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን ዘሩባቤል፥ ኢያሱና የጐሣ መሪዎች ሁሉ እነዚህን ሰዎች፦ “ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ስለምንሠራው ቤተ መቅደስ የእናንተ ርዳታ አያስፈልገንም፤ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት ቂሮስ ባዘዘን መሠረት እኛው ራሳችን እንሠራዋለን” ሲሉ መለሱላቸው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዘሩ​ባ​ቤ​ልና ኢያ​ሱም፥ የቀ​ሩ​ትም የእ​ስ​ራ​ኤል አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች፥ “የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ቤት መሥ​ራት ለእ​ኛና ለእ​ና​ንተ አይ​ደ​ለም፤ እኛ ራሳ​ችን ግን የፋ​ርስ ንጉሥ ቂሮስ እን​ዳ​ዘ​ዘን ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እን​ሠ​ራ​ለን” አሉ​አ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዘሩባቤልና ኢያሱም የቀሩትም የእስራኤል አባቶች ቤቶች አለቆች “የአምላካችንን ቤት መሥራት ለእኛና ለእናንተ አይደለም፤ እኛ ለብቻችን ግን የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዳዘዘን ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤት እንሠራለን” አሉአቸው።

Ver Capítulo



ዕዝራ 4:3
16 Referencias Cruzadas  

በኤርምያስም አንደበት የተነገረው የጌታ ቃል እንዲፈጸም በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት ጌታ የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አስነሣ፤ እርሱም በመንግሥቱ ሁሉ አዋጅ ነገረ፥ ደግሞም በጽሑፍ እንዲህ ብሎ አወጀ፦


በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት፥ በኤርምያስ አፍ የተናገረው የጌታ ቃል እንዲፈጸም፥ ጌታ የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አስነሣ፥ ይህም በመንግሥቱ ሁሉ በአዋጅና በጽሑፍ እንዲያስነግር ነው፤


የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፦ “የሰማያት አምላክ ጌታ የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፥ በይሁዳም ባለችው በኢየሩሳሌም ቤት እንድሠራለት አዝዞኛል፤


ከሕዝቡ ሁሉ ማንም በእናንተ ውስጥ የሚኖር አምላኩ ከእርሱ ጋር ይሁን፥ እርሱም በይሁዳ ወዳለችው ወደ ኢየሩሳሌም ይውጣ፥ የጌታ የእስራኤል አምላክን ቤት ይሥራ፥ እርሱም በኢየሩሳሌም ያለ አምላክ ነው፤


በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በመጡ በሁለተኛው ዓመት በሁለተኛውም ወር የሸአልቲኤል ልጅ ዘሩባቤል፥ የዮፃዳቅም ልጅ ኢያሱ፥ የቀሩትም ወንድሞቻቸው ካህናትና ሌዋውያን፥ ወደ ኢየሩሳሌምም የተመለሱት ምርኮኞች ሁሉ፥ ሌዋውያንንም ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ የጌታን ቤት ሥራ እንዲቆጣጠሩ መረጧቸው።


እኔም፦ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም አገልጋዮቹ እንነሳለን፥ እንሠራለንም፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም ድርሻ ወይም መብት ወይም መታሰቢያ የላችሁም” ብዬ መለስኩላቸው።


ቂሮስንም፦ “እርሱ እረኛዬ ነው”፤ እርሱም ኢየሩሳሌምን፦ “ትታነጺያለሽ ቤተ መቅደስም ይመሠረታል” ይላል፤ እኔም “ፈቃዴን ሁሉ ይፈጽማል” እላለሁ።


ስለ አገልጋዬ ስለ ያዕቆብ፥ ስለ መረጥሁትም ስለ እስራኤል ብዬ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ በቁልምጫ ስምህ ጠራሁህ፥ አንተ ግን አላወቅኸኝም።


“እነሆ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ብልሆች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።


ስለዚህ ሳምራዊቲቱ “አንተ የይሁዳ ሰው ስትሆን ሳምራዊት ሴት ከምሆን ከእኔ መጠጥ እንዴት ትለምናለህ?” አለችው፤ አይሁድ ከሳምራውያን ጋር አይተባበሩም ነበርና።


ልብህ በእግዚአብሔር ፊት የቀና አይደለምና ከዚህ ነገር ዕድል ወይም ፈንታ የለህም።