ዕዝራ 4:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ወደ ዘሩባቤልና ወደ አባቶች አለቆች ቀርበው፦ “እንደ እናንተ አምላካችሁን እንፈልገዋለን፥ የአሦር ንጉሥ ኤሳርሐዶን ወደዚህ ካመጣን ቀን ጀምሮ ለእርሱ እንሠዋ ነበርና፥ ከእናንተ ጋር እንሥራ” አሉአቸው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ወደ ዘሩባቤልና ወደ ቤተ ሰቡ አለቆች መጥተው፣ “እኛም እንደ እናንተ አምላካችሁን የምንፈልግ ነን፤ የአሦር ንጉሥ አስራዶን ወደዚህ ካመጣን ጊዜ ጀምሮ ለርሱ ስንሠዋለት ቈይተናል፤ ስለዚህ ዐብረን ከእናንተ ጋራ እንሥራ” አሏቸው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 ወደ ዘሩባቤልና ወደ ጐሣ መሪዎችም ቀርበው “ቤተ መቅደሱን ከእናንተ ጋር አብረን እንሥራ፤ ይህንኑ እናንተ የምታመልኩትን እግዚአብሔር እኛም እናመልከዋለን፤ የአሦር ንጉሠ ነገሥት አስራዶን ወደዚህ አገር ከላከንም ጊዜ ጀምሮ መሥዋዕት ስናቀርብለት ቈይተናል” አሉአቸው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ወደ ዘሩባቤልና ወደ አባቶች ቤቶች አለቆችም ቀርበው፥ “የአሦር ንጉሥ አስራዶን ወደዚህ ካመጣን ቀን ጀምሮ ለአምላካችሁ እንሠዋለንና፥ እንደ እናንተም እንፈልገዋለንና ከእናንተ ጋር እንሥራ” አሉአቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ወደ ዘሩባቤልና ወደ አባቶች ቤቶች አለቆች ቀርበው “የአሦር ንጉሥ አስራዶን ወደዚህ ካመጣን ቀን ጀምሮ ለአምላካችሁ እንሠዋለንና፥ እንደ እናንተም እንፈልገዋለንና ከእናንተ ጋር እንሥራ” አሉአቸው። Ver Capítulo |