ኢሳይያስ 44:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)28 ቂሮስንም፦ “እርሱ እረኛዬ ነው”፤ እርሱም ኢየሩሳሌምን፦ “ትታነጺያለሽ ቤተ መቅደስም ይመሠረታል” ይላል፤ እኔም “ፈቃዴን ሁሉ ይፈጽማል” እላለሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም28 ቂሮስንም፣ ‘እርሱ እረኛዬ ነው፤ ፈቃዴን ሁሉ ይፈጽማል፤ ኢየሩሳሌምም፣ “እንደ ገና ትሠራ፣” ቤተ መቅደሱም፣ “መሠረቱ ይጣል” ይላል’ እላለሁ።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም28 ቂሮስን ‘የመንጋዬ እረኛ ነህ፤ ዕቅዴን ሁሉ ትፈጽማለህ’ እለዋለሁ፤ ኢየሩሳሌምን ‘አንቺ እንደገና ትገነቢአለሽ’ ቤተ መቅደሱን፥ ‘መሠረትህ ይጣላል’ እላቸዋለሁ።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)28 ቂሮስንም፥ “ብልህ ሁን፤ እርሱም ኢየሩሳሌምን፦ ትታነጺያለሽ ቤተ መቅደስንም እመሠርታለሁ ብሎ ፈቃዴን ሁሉ ይፈጽማል” ይላል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)28 ቂሮስንም፦ እርሱ እረኛዬ ነው፥ እርሱም ኢየሩሳሌምን፦ ትታነጺያለሽ ቤተ መቅደስም ይመሠረታል ብሎ ፈቃዴን ሁሉ ይፈጽማል እላለሁ። Ver Capítulo |