La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዕዝራ 3:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢያሱ፥ ልጆቹ፥ ወንድሞቹ፥ የይሁዳም ልጆች ቃድሚኤልና ልጆቹ፥ የሔናዳድም ልጆች፥ ልጆቻቸውና ወንድሞቻቸው ሌዋውያንም የእግዚአብሔርን ቤት የሚሠሩትን እንዲቆጣጠሩ እንደ አንድ ቆሙ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢያሱ፣ ወንዶች ልጆቹና ወንድሞቹ፣ የዮሖዳያ ዘሮች ቀድምኤልና ወንዶች ልጆቹ፣ የኤንሐዳድ ወንዶች ልጆች፣ ልጆቻቸውና ወንድሞቻቸው፣ ሌዋውያኑም ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤት የሚሠሩትን ሰዎች ለመቈጣጠር በአንድ ላይ ሆኑ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሌዋዊው ኢያሱና ወንዶች ልጆቹ፥ እንዲሁም ዘመዶቹ፥ ቃድሚኤልና ከሖዳዊያ ቤተሰብ ወገን የሆኑ ወንዶች ልጆቹም ሁሉ በአንድነት ተባብረው ቤተ መቅደሱን እንደገና የመሥራቱን ኀላፊነት ተረከቡ፤ የሔናዳድ ዘሮች የሆኑት ሌዋውያንም ይረዱአቸው ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢያ​ሱም፥ ልጆ​ቹም ተሾሙ፤ ወን​ድ​ሞ​ቹም፥ የይ​ሁ​ዳም ልጆች ቀደ​ም​ያ​ልና ልጆቹ፥ የኢ​ን​ሐ​ዳ​ድም ልጆች፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ውና ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ሌዋ​ው​ያ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት የሚ​ሠ​ሩ​ትን ያሠሩ ዘንድ በአ​ን​ድ​ነት ቆሙ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢያሱ፥ ልጆቹና ወንድሞቹ፥ የይሁዳም ልጆች ቀድምኤልና ልጆቹ፥ የኤንሐዳድም ልጆች፥ ልጆቻቸውና ወንድሞቻቸው፥ ሌዋውያንም የእግዚአብሔርን ቤት የሚሠሩትን ያሠሩ ዘንድ በአንድነት ቆሙ።

Ver Capítulo



ዕዝራ 3:9
6 Referencias Cruzadas  

ከእነዚህም ውስጥ የጌታን ቤት ሥራ የሚሠሩት ሀያ አራት ሺህ ነበሩ። ስድስቱ ሺህም አለቆችና ፈራጆች ነበሩ።


ሰዎቹም ሥራውን በታማኝነት ሠሩ፤ በእነርሱም ላይ የተሾሙት፥ ሥራውንም የሚሠሩት ሌዋውያን ከሜራሪ ልጆች ኢኤትና አብድዩ፥ ከቀዓትም ልጆች ዘካርያስና ሜሱላም ነበሩ። ከሌዋውያንም ወገን በዜማ ዕቃ አዋቂዎች የነበሩ ሁሉ


ሌዋውያኑ፥ ከሆዳቭያ ወገን የኢያሱና የቃድምኤል ልጆች፥ ሰባ አራት።


በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በመጡ በሁለተኛው ዓመት በሁለተኛውም ወር የሸአልቲኤል ልጅ ዘሩባቤል፥ የዮፃዳቅም ልጅ ኢያሱ፥ የቀሩትም ወንድሞቻቸው ካህናትና ሌዋውያን፥ ወደ ኢየሩሳሌምም የተመለሱት ምርኮኞች ሁሉ፥ ሌዋውያንንም ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ የጌታን ቤት ሥራ እንዲቆጣጠሩ መረጧቸው።


ከእርሱም በኋላ የሔናዳድ ልጅ ቢኑይ ከዓዛርያ ቤት ጀምሮ እስከ የግንቡ መደገፊያ ድረስ ሌላውን ክፍል አደሰ።


ሌዋውያኑ፥ የሆድዋ ወገን የኢያሱና የቃድሚኤል ልጆች፥ ሰባ አራት።