La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዕዝራ 2:70 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ ከሕዝቡም አንዳንዶች፥ መዘምራኑ፥ በር ጠባቂዎቹና፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ፥ በከተሞቻቸው፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ መዘምራኑ፣ በር ጠባቂዎቹና የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፣ ከሌሎች ሰዎች ጋራ በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ፤ የቀሩት እስራኤላውያንም በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ካህናቱ፥ ሌዋውያኑና ከሕዝቡም አንዳንዱ በኢየሩሳሌም ወይም በአቅራቢያዋ ሰፈሩ፤ መዘምራኑ፥ የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎችና ለቤተ መቅደሱ ሕንጻ የተመደቡት ሠራተኞች በየአቅራቢያው በሚገኙት ከተሞች ሰፈሩ፤ እንዲሁም የቀሩት እስራኤላውያን የቀድሞ አባቶቻቸው በነበሩባቸው ከተሞች ሰፈሩ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ ከሕ​ዝ​ቡም አያ​ሌ​ዎች፥ መዘ​ም​ራ​ኑና በረ​ኞ​ቹም፥ ናታ​ኒ​ምም በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ተቀ​መጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ካህናቱና ሌዋውያኑ፥ ከሕዝቡም አያሌዎች፥ መዘምራኑና በረኞቹ፥ ናታኒምም በከተሞቻቸው፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ።

Ver Capítulo



ዕዝራ 2:70
7 Referencias Cruzadas  

ከዚያም በኋላ ከሶርያውያን ሰፈር በመነሣት ወደ ሰማርያ ተመልሰው ሄዱ፤ እዚያም እንደ ደረሱ የከተማይቱን ቅጽር በር ዘበኞች ጠርተው “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄደን ነበር፤ ነገር ግን ምንም ያየነው ሰው ወይም የሰማነው ድምፅ እንኳ የለም፤ ፈረሶችና አህዮች እንደ ታሰሩ ናቸው፤ ድንኳኖቹም ሶርያውያን ትተዋቸው ስለ ሄዱ ባዶአቸውን ናቸው” ሲሉ ነገሩአቸው።


አስቀድሞ ሳኦል ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስራኤልን የምታወጣና የምታገባ አንተ ነበርህ፤ ጌታ አምላክህም፦ ‘ሕዝቤን እስራኤልን አንተ ትጠብቃለህ፤ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ አለቃ ትሆናለህ’ ብሎህ ነበር።”


በአውራጃዎቻቸውና በከተሞቻቸው መጀመሪያ የተቀመጡ እስራኤልና ካህናት ሌዋውያንም የቤተ መቅደሱም አገልጋዮች ነበሩ።


የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው።