አለቆቻችንም ለጉባኤው ሁሉ ይቁሙ፥ ስለዚህም ነገር የአምላካችን የነደደው ቁጣ ከእኛ እንዲመለስ፥ እያንዳንዳቸው በከተሞቻችን ያሉ እንግዶቹን ሴቶች ያገቡት ሁሉ በተቀጠረው ጊዜ ይምጡ፥ ከእነርሱም ጋር የከተማ ሽማግሌዎችና ፈራጆች ይምጡ።”
ዕዝራ 10:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዐሣሄል ልጅ ዮናታንና የቲቅዋ ልጅ ያሕዝያ ብቻ ይህን ነገር ተቃወሙ፤ ምሹላምና ሌዋዊውም ሻብታይ ደገፏቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህንም ነገር የተቃወሙት ከሜሱላምና ከሌዋዊው ከሳባታይ ድጋፍ ያገኙት የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሕዝያ ብቻ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም በተነገረ ጊዜ መሹላምና ሻበታይ ተብሎ የሚጠራው አንድ ሌዋዊ ድጋፍ ከሰጡአቸው ከዐሣሔል ልጅ ዮናታንና የቲቅዋ ልጅ ከሆነው ከያሕዘያ በቀር ሌላ ተቃዋሚ አልነበረም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሐዝያ ስለዚህ ነገር ከእኔ ጋር ናቸው፤ ሜሱላምና ሌዋዊው ሰባታይም ይረዱአቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሕዝያ ይህን ነገር ተቃወሙ፤ ሜሱላምና ሌዋዊዉ ሳባታይ ረዱአቸው። |
አለቆቻችንም ለጉባኤው ሁሉ ይቁሙ፥ ስለዚህም ነገር የአምላካችን የነደደው ቁጣ ከእኛ እንዲመለስ፥ እያንዳንዳቸው በከተሞቻችን ያሉ እንግዶቹን ሴቶች ያገቡት ሁሉ በተቀጠረው ጊዜ ይምጡ፥ ከእነርሱም ጋር የከተማ ሽማግሌዎችና ፈራጆች ይምጡ።”
ምርኮኞቹም እንዲህ አደረጉ፥ ካህኑ ዕዝራ፥ የአባቶችን መሪዎች መረጠ፤ በየአባቶቻቸው ቤቶች ተለዩ፥ ሁሉም በየስማቸው ተጻፉ፥ በአሥረኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ነገሩን ሊመረምሩ ተቀመጡ።