ዕዝራ 1:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዙሪያቸውም ያሉ ሁሉ በፈቃዳቸው ካቀረቡት መባ ሁሉ በተጨማሪ በእጃቸው፥ በብር ዕቃና በወርቅ፥ በዕቃዎችና በእንስሶችና በውድ ነገሮች አበረታቱአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጎረቤቶቻቸውም ሁሉ በበጎ ፈቃድ ከሰጡት መባ በተጨማሪ ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ዕቃዎችን፣ ቍሳቍስን፣ እንስሳትንና ሌሎች ጠቃሚ የሆኑ ስጦታዎችንም በመለገስ ረዷቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጐረቤቶቻቸውም ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ዕቃዎችን፥ ቈሳቊሶችንና ከብቶችን፥ ሌሎችንም ጠቃሚ የሆኑ ስጦታዎችና በቤተ መቅደስ መባ ሆኖ የሚቀርብ ሌላም ነገር በመለገሥ ረዱአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዙሪያቸውም ያሉ ሁሉ በፈቃዳቸው ካቀረቡት ሁሉ ሌላ በብር ዕቃና በወርቅ፥ በገንዘቦችና በእንስሶች፥ በሌላም ስጦታ ይረዷቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዙሪያቸውም ያሉ ሁሉ በፈቃዳቸው ካቀረቡት ሁሉ ሌላ በብር ዕቃና፥ በወርቅ፥ በቍሳቍሶችና በእንስሶች በሌላም ስጦታ አገዙአቸው። |
ከሁሉም ስፍራዎች የተረፈው ሁሉ መፃተኛ ሆኖ በሚኖርበት የሰፈሩ ሰዎች በብርና በወርቅ በዕቃም በእንስሳም ይርዱት፥ ይህም በኢየሩሳሌም ላለው ለእግዚአብሔር ቤት በፈቃዳቸው ከሚያቀርቡት መባ ጋር ይሁን።”
በአራተኛውም ቀን ብሩ፥ ወርቁና ዕቃዎቹም በአምላካችን ቤት በካህኑ በኡሪያ ልጅ በምሬሞት እጅ ተመዘነ፤ ከእርሱም ጋር የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር ነበረ። ከእነርሱም ጋር ሌዋውያኑ የኢያሱ ልጅ ዮዛባድና የቢኑይ ልጅ ኖዓድያ ነበሩ።