ዕዝራ 1:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወርቁና የብሩ ዕቃዎች ሁሉ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ፤ እነዚህንም ሁሉ ሼሽባጻር ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም ከተመለሱ ምርኮኞቹ ጋር ወሰደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአጠቃላይ ዐምስት ሺሕ አራት መቶ የወርቅና የብር ዕቃዎች ነበሩ። ሰሳብሳር ምርኮኞቹ ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሱ ይህን ሁሉ ዕቃ ይዞ ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሼሽባጻር ከሌሎቹ ስደተኞች ጋር ሆኖ ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም በተመለሰ ጊዜ ያመጣቸው ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ዕቃዎች ድምር 5400 ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወርቁና የብሩ ዕቃዎች ሁሉ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ፤ እነዚህንም ሁሉ ሲሳብሳር ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም ከተመለሱ ምርኮኞች ጋር ወሰደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወርቁና የብሩ ዕቃዎች ሁሉ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ፤ እነዚህንም ሁሉ ሰሳብሳር ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም ከተመለሱ ምርኮኞቹ ጋር ወሰደ። |
የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው።