ሰዎቹም ከዚያ ተነሥተው እስከ ዮርዳኖስ ወንዝ ድረስ ዘልቀው ሄዱ፤ በየመንገዱም ሶርያውያን ሲሸሹ ጥለውት የሄዱትን ልብስና መሣሪያ ሁሉ አዩ፤ ከዚያም በኋላ ተመልሰው መጥተው ይህን ሁሉ ለንጉሡ ነገሩ።
ሕዝቅኤል 7:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብራቸውን በጎዳናዎቹ ላይ ይጥላሉ፥ ወርቃቸውም እንደ ርኩስ ነገር ይቆጠራል፥ በጌታ የመዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም። አይጠግቡም፥ ሆዳቸውንም አይሞሉም፥ የኃጢአታቸው ዕንቅፋት ሆኖአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ብራቸውን በየጐዳናው ይጥላሉ፤ ወርቃቸውም እንደ ርኩስ ነገር ይቈጠራል። በእግዚአብሔር የቍጣ ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ በኀጢአት እንዲወድቁ ዕንቅፋት ሆኖባቸዋልና በልተው አይጠግቡበትም፤ ሆዳቸውንም አይሞሉበትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብራቸውን በየመንገዱ ላይ ይወረውራሉ፤ ወርቃቸውም እንደ ርኩስ ነገር ይቈጠራል፤ ብርና ወርቃቸው በእግዚአብሔር ቊጣ ቀን አያድኑአቸውም፤ ራባቸውን አያስወግዱላቸውም፤ ወይም ሆዳቸውን አይሞሉላቸውም፤ በኃጢአት ለመውደቃቸው ምክንያት የሆኑባቸው እነርሱ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብራቸውን በጎዳናዎቹ ላይ ይጥላሉ፤ ወርቃቸውም ይረክሳል፤ በእግዚአብሔር መዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው አያድናቸውም። እርሱ የኀጢአታቸው እንቅፋት ሆኖአልና ሰውነታቸውን አያጠግቡም፤ ሆዳቸውንም አይሞሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብራቸውን በጎዳናዎቹ ላይ ይጥላሉ ወርቃቸውም እንደ ጕድፍ ይሆናል፥ በእግዚአብሔር መዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ያድናቸው ዘንድ አይችልም። እርሱ የኃጢአታቸው ዕንቅፋት ሆኖአልና ሰውነታቸውን አያጠግቡም ሆዳቸውንም አይሞሉም። |
ሰዎቹም ከዚያ ተነሥተው እስከ ዮርዳኖስ ወንዝ ድረስ ዘልቀው ሄዱ፤ በየመንገዱም ሶርያውያን ሲሸሹ ጥለውት የሄዱትን ልብስና መሣሪያ ሁሉ አዩ፤ ከዚያም በኋላ ተመልሰው መጥተው ይህን ሁሉ ለንጉሡ ነገሩ።
በብርም የተለበጡትን የተቀረጹትን ምስሎችህን፥ በወርቅም የተለበጡትን ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎችህን ታረክሳለህ፤ እንደ ርኩስም ነገር ትጥላቸዋለህ፦ “ከእኔ ራቁ!” ትላቸዋለህ።
እንጀራ ላልሆነ ነገር ገንዘብን ለምን ታባክናላችሁ፥ የድካማችሁንም ዋጋ በማያጠግብ ነገር ለምን ትለውጣላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው።
ማንም ከእስራኤልም ቤት፥ በእስራኤልም የሚቀመጥ መጻተኛ፥ ራሱን ከእኔ የሚለይ፥ ጣዖቶቹን በልቡ የሚያኖር፥ የበደሉንም የማሰናከያ ድንጋይ በፊቱ የሚያቆም፥ ስለ እኔም ለመጠየቅ ወደ ነቢዩ የሚመጣ፥ እኔ ጌታ ራሴ እመልስለታለሁ፥
በጣዖቶቻቸው ፊት አገልግለዋቸው ነበሩና፥ ለእስራኤልም ቤት የኃጢአት ዕንቅፋት ሆነዋልና ስለዚህ እጄን በላያቸው አንሥቻለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይሸከማሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
በጌታ የመዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች፥ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ አስፈሪ ፍፃሜ ያመጣባቸዋልና።
ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፥ የሰማይን ወፎችና የባሕርን ዓሦች አጠፋለሁ፥ ክፉዎች እንዲደናቀፉ አደርጋለሁ፥ ሰውንም ከምድር ገጽ እቆርጣለሁ ይላል ጌታ።