ሕዝቅኤል 7:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጊዜው መጥቷል፥ ቀኑ ቀርቧል፥ የሚገዛ ደስ አይበለው የሚሸጥም አያልቅስ፥ ቁጣ ብዙዎች ሁሉ ላይ ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጊዜው ደርሷል፤ ቀኑም ይኸው! መዓት በሕዝቡ ሁሉ ላይ ስለ መጣ፣ የሚገዛ አይደሰት፤ የሚሸጥም አይዘን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ ጊዜው ደርሶአል፤ ቀኑም ቀርቦአል፤ የእኔ የእግዚአብሔር ቊጣ በሁሉም ላይ ስለሚመጣ ገዢ አይደሰት፤ ሻጭም አይዘን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጊዜው መጥቶአል፤ ቀኑ እነሆ ቀርቦአል፤ መቅሠፍቷ በሁለንተናዋ መልቶአልና የሚገዛ ደስ አይበለው፤ የሚሸጥም አይዘን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጊዜው መጥቶአል፥ ቀኑ ቀርቦአል፥ መዓት በብዙዎች ሁሉ ላይ ነውና የሚገዛ ደስ አይበለው የሚሸጥም አያልቅስ። |
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ቁጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ፥ በሰውና በእንስሳ ላይ፥ በዱር ዛፎችና በምድር ፍሬ ላይ ይወርዳል፤ ይነድዳል፥ አይጠፋምም።”
ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህን ምሳሌ አስቀረዋለሁ በእስራኤልም ዘንድ ደግሞ ምሳሌ አድርገው አይናገሩትም፥ አንተ ግን፦ ዘመኑና የራእዩ ሁሉ ነገር ቀርቧል በላቸው።