Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 7:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እነሆ ቀኑ፥ እነሆ መጥቷል፥ ፍጻሜህ መጥቷል፥ ብትሩ አብቧል፥ ትዕቢትም አቆጥቁጦአል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “ ‘እነሆ ቀኑ ይኸው ደረሰ! የጥፋት ፍርድ ተገልጧል፤ በትሩ አቈጥቍጧል፤ ትዕቢት አብቧል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እነሆ፥ የጥፋት ቀን በእስራኤል ላይ ሊመጣ ተቃርቦአል፤ ግፍና ዐመፅ በዝቶአል፤ ትዕቢትም ከፍ ከፍ ብሎአል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 “እነሆ ቀኑ ደር​ሶ​አል፤ እነሆ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ወጥ​ታ​ለች፤ ስብ​ራ​ትህ ደር​ሶ​አል፤ ብት​ርም አብ​ባ​ለች፤ ስድ​ብም በዝ​ቶ​አል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እነሆ ቀኑ፥ እነሆ፥ መጥቶአል፥ ተራህ ወጥቶአል፥ ብትር አብቦአል፥ ትዕቢትም አጅብጅፎአል።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 7:10
19 Referencias Cruzadas  

የቁጣዬ በትር ለሆነ፤ የመቅሠፍቴም ዱላ በእጁ ላለው ለአሦራዊው ወዮለት!


ስለዚህ፥ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” እንደሚል፥ የሚሰጠው ጸጋ ግን ከሁሉም ይበልጣል።


እነርሱም፦ “ሰላምና ደኅንነት ነው” በሚሉ ጊዜ ምጥ እንደ ያዛት እርጉዝ ሴት ድንገተኛ ጥፋት በእነርሱ ላይ ይመጣባቸዋል፤ ከቶም አያመልጡም።


በሰነፍ አፍ የትዕቢት በትር አለ፥ የጠቢባን ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች።


እንዲህም ሆነ፤ በማግስቱ ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገባ፤ እነሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆነው የአሮን በትር አቈጥቁጦ፥ እምቡጥም አውጥቶ፥ አበባም አብቦ፥ የበሰለ ለውዝም አፍርቶ ነበር።


ፈተና ተደርጓል፥ ደግሞ የተናቀ በትር ባይኖርስ ምን ይሆናል? ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


እንዲገድል ተስሎአል እንዲያብረቀርቅም ተወልውሏል፥ እኛስ ደስ ይለናልን? የልጄን በትር እንደ ማንኛውም ዛፍ ንቆታል።


ከቅርንጫፍዋ እሳት ወጣች፥ ፍሬዋንም በላች፥ ለገዢዎች በትረ መንግሥት የሚሆን ብርቱ ቅርንጫፍ በእርሷ ዘንድ የለም። ይህ ሙሾ ነው፥ ለልቅሶም ይሆናል።


ፍጻሜ መጥቷል፥ ፍጻሜ መጥቷል፥ በአንቺ ላይ ነቅቷል፥ እነሆ፥ መጥቷል።


ለኤፍሬም ሰካራሞች የመታበያ አክሊል ለሆነች፥ በወይን ጠጅ ለተሸነፉ፥ በለምለሙ ሸለቆአቸው ራስ ላይ ላለችም ለረገፈች ለክብሩ ጌጥ አበባ ወዮላት!


ትዕቢት ጥፋትን፥ ኩሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል።


ሥርዓቴንም ቢያረክሱ፥ ትእዛዜንም ባይጠብቁ፥


ዓይኔም አይራራም፥ እኔም አላዝንም፥ መንገድሽን በአንቺ ላይ እመልስብሻለሁ፥ ርኩሰቶችሽም በመካከልሽ ይሆናሉ፥ የምቀሥፍም እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


ጊዜው መጥቷል፥ ቀኑ ቀርቧል፥ የሚገዛ ደስ አይበለው የሚሸጥም አያልቅስ፥ ቁጣ ብዙዎች ሁሉ ላይ ነውና።


ጉበኛውም፦ “ይነጋል ደግሞም ይመሻል፤ ትጠይቁ ዘንድ ብትወድዱ ጠይቁ፤ ተመልሳችሁም ኑ” አለ።


ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህን ምሳሌ አስቀረዋለሁ በእስራኤልም ዘንድ ደግሞ ምሳሌ አድርገው አይናገሩትም፥ አንተ ግን፦ ዘመኑና የራእዩ ሁሉ ነገር ቀርቧል በላቸው።


ቀኑ ቅርብ ነውና፥ የጌታ ቀን ቅርብ ነው፥ የደመና ቀን፥ የሕዝቦች ጊዜ ይሆናል።


የጌታ ቀን ቀርቧልና ለቀኑ ወዮ! እርሱም ሁሉን ከሚችል ከአምላክ ዘንድ እንደ ጥፋት ይመጣል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios