ሰውዬውም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፥ በዓይንህ እይ፥ በጆሮህም ስማ፥ የማሳይህን ሁሉ ልብ ብለህ አስተውል፥ ይህን እንዳሳይህ ወደዚህ ተመርተሃልና የምታየውንም ሁሉ ለእስራኤል ቤት ንገር።”
ሕዝቅኤል 47:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ አይተሃልን? መራኝ፥ ወደ ወንዙም ዳር መለሰኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ ይህን ታየዋለህን?” ሲል ጠየቀኝ። ከዚያም መልሶ ወደ ወንዙ ዳር መራኝ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውየውም “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን ሁሉ በጥንቃቄ አስታውስ” አለኝ። ከዚያን በኋላ ያ ሰው ወደ ውሃው ዳርቻ መለሰኝ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! አይተሃልን?” አለኝ። አመጣኝም፤ ወደ ወንዙም ዳር መለሰኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ አይተሃልን? አለኝ። አመጣኝም፥ ወደ ወንዙም ዳር መለሰኝ። |
ሰውዬውም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፥ በዓይንህ እይ፥ በጆሮህም ስማ፥ የማሳይህን ሁሉ ልብ ብለህ አስተውል፥ ይህን እንዳሳይህ ወደዚህ ተመርተሃልና የምታየውንም ሁሉ ለእስራኤል ቤት ንገር።”
ጌታም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ጌታ ቤት ሥርዓት ሁሉ እና ሕጉን ሁሉ የምናገርህን ሁሉ ልብ አድርግ በዓይንህ ተመልከት በጆሮህም ስማ፤ የቤቱን መግቢያ የመቅደሱንም መውጫ ሁሉ ልብ አድርግ።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ ይህን አይተሃልን? በዚህ የሰሩትን ርኩሰት ሊያደርጉ ለይሁዳ ቤት ይህ ቀላል ነገር ነውን? ምድሪቱን በዓመፅ ሞልተዋታል፥ ሊያስቆጡኝም ተመልሰዋል፥ እነሆ ቅርንጫፉን ወደ አፍንጫቸው አቅርበዋል።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ ከመቅደሴ ሊያርቁኝ፥ የእስራኤል ቤት በዚህ የሚፈጽሙትን ታላቅ ርኩሰት ታያለህን? ደግሞም ተመልሰህ ከዚህ የበለጠ ታላቅ ርኩሰት ታያለህ።
እርሱም፦ “የምታየው ምንድነው?” አለኝ። እኔም፦ “እነሆ፥ ሁለንተናው ወርቅ የሆነ መቅረዝ ይታየኛል፤ የዘይት ማሰሮም በላዩ ላይ ነበረ። በመቅረዙም ላይ ሰባት ቧንቧዎች ያሏቸው ሰባት መብራቶች ነበሩ።
እርሱም፦ “የምታየው ምንድነው?” አለኝ። እኔም፦ “በራሪ የመጽሐፍ ጥቅልል አያለሁ፤ ርዝመቱ ሀያ ክንድ ወርዱም ዐሥር ክንድ ነው” አልኩት።