ሕዝቅኤል 47:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰሜኑ በር በኩል አወጣኝ፤ በውጭ ባለው መንገድ፥ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከት በውጭ ወዳለው በር አመጣኝ፤ እነሆ ውኃው በደቡብ በኩል ይፈስስ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በሰሜኑ በር በማውጣት በውጭ አዙሮ በምሥራቅ አቅጣጫ ወዳለው የውጭ በር መራኝ፤ ውሃውም በደቡብ በኩል ይፈስስ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያም ሰው በሰሜኑ ቅጽር በር በኩል ከቤተ መቅደሱ አውጥቶ ወሰደኝ፤ ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ በሚመለከተውም ቅጽር በር አዞረኝ፤ ከቅጽር በሩም በስተ ደቡብ ውሃው ወደ ምሥራቅ ይፈስ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰሜኑም በር በኩል አወጣኝ፤ በስተ ውጭ በአለው መንገድ፥ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከት በስተ ውጭ ወዳለው በር አዞረኝ፤ እነሆም ውኃው በቀኝ በኩል ይፈስስ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰሜኑም በር በኩል አወጣኝ፥ በስተ ውጭ ባለው መንገድ፥ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከት በስተ ውጭ ወዳለው በር አዞረኝ፥ እነሆም፥ ውኃው በቀኙ ወገን ይፈስስ ነበር። |
ወደ ቤቱ መግቢያ መለሰኝ፤ እነሆ ውኃ ከቤቱ መድረክ በታች ወደ ምሥራቅ ይወጣ ነበር፥ የቤቱ ፊት ወደ ምሥራቅ ይመለከት ነበርና፤ ውኃውም ከቤቱ በስተ ቀኝ በኩል በታች በመሠዊያው በደቡብ በኩል ይወርድ ነበር።