Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 47:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሰውዬው ገመድ በእጁ ይዞ ወደ ምሥራቅ ወጣ፥ አንድ ሺህ ክንድ ለካ፥ በውኃውም ውስጥ አሳለፈኝ፥ ውኃውም እስከ ቁርጫምጭሚት ድረስ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ያም ሰው የመለኪያውን ገመድ በእጁ ይዞ ወደ ምሥራቅ በመሄድ፣ አንድ ሺሕ ክንድ ለካ፤ ከዚያም እስከ ቍርጭምጭሚት በሚደርሰው ውሃ ውስጥ መራኝ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ያም ሰው በያዘው የመለኪያ ገመድ ወደ ምሥራቅ የሚፈሰውን ውሃ በመከተል አንድ ሺህ ክንድ ለካ፤ በዚያም ውሃ እየተራመድኩ እንድሻገር አደረገኝ፤ ውሃውም እስከ ቊርጭምጭሚቴ ደረሰ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሰው​ዮ​ውም የመ​ለ​ኪያ ገመድ በእጁ ይዞ ወደ ምሥ​ራቅ ወጣ፤ አንድ ሺህም ክንድ ለካ፤ በው​ኃ​ውም ውስጥ አሻ​ገ​ረኝ፤ ውኃ​ውም እስከ ቍር​ጭ​ም​ጭ​ሚት ደረሰ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሰውዬውም ገመዱን በእጁ ይዞ ወደ ምሥራቅ ወጣ አንድ ሺህም ክንድ ለካ፥ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃም እስከ ቍርጫምጭሚት ደረሰ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 47:3
12 Referencias Cruzadas  

ወደዚያም አመጣኝ፥ እነሆ፥ መልኩ ናስ የመሰለ አንድ ሰው በዚያ ነበረ፥ በእጁም የተልባ እግር ገመድና የመለኪያ ዘንግ ይዞ ነበረ፤ እርሱም በበሩ አጠገብ ቆሞ ነበር።


በሰሜኑ በር በኩል አወጣኝ፤ በውጭ ባለው መንገድ፥ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከት በውጭ ወዳለው በር አመጣኝ፤ እነሆ ውኃው በደቡብ በኩል ይፈስስ ነበር።


እንደገና አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሳለፈኝ፥ ውኃውም እስከ ጉልበት ድረስ ነበር። ደግሞም አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሳለፈኝ፥ ውኃውም እስከ ወገብ ድረስ ነበር።


ዐይኖቼንም አንሥቼ እነሆም አራት ቀንዶች አየሁ።


ዐይኖቼንም አነሣሁ፥ እነሆም፥ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ አንድ ሰውን አየሁ።


እነሆም፥ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በዚህች ከተማ ቆዩ።”


ስለዚህ በእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ ብሎና የመንፈስ ቅዱስን የተስፋ ቃል ከአብ ተቀብሎ ይህን እናንተ አሁን የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰው።


በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፤ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።


በትር የሚመስል የመለኪያ ሸንበቆ ተሰጠኝ፤ እንዲህም ተባልሁ “ተነሥተህ የእግዚአብሔርን መቅደስና መሠዊያውን በዚያም የሚሰግዱትን ለካ።


የተናገረኝም ከተማይቱንና ደጆችዋን ቅጥርዋንም ይለካ ዘንድ የወርቅ ዘንግ ነበረው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos