ሕዝቅኤል 43:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያየሁትም ራእይ ከተማይቱን ለማጥፋት በመጣሁ ጊዜ እንዳየሁት ራእይ ነበረ፤ ራእዩም በኮቦር ወንዝ እንዳየሁት ራእይ ነበረ፤ እኔም በግምባሬ ተደፋሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያየሁትም ራእይ ከተማዪቱን ለማጥፋት በመጣ ጊዜ ያየሁትን ራእይ የሚመስልና እንዲሁም በኮቦር ወንዝ ካየሁት ራእይ ጋራ የሚመሳሰል ነበር፤ እኔም በግንባሬ ተደፋሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ራእይ ከዚህ በፊት እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት በመጣ ጊዜ ያየሁትን ይመስል ነበር፤ በኬባር ወንዝ አጠገብ ካየሁትም ራእይ ጋር ይመሳሰላል፤ በዚያን ጊዜ በግንባሬ ተደፋሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያየሁትም ራእይ ከተማዪቱን ለማጥፋት በመጣሁ ጊዜ እንደ አየሁት ራእይ ነበረ፤ ራእዩም በኮቦር ወንዝ እንደአየሁት ራእይ ነበረ፤ እኔም በግምባሬ ተደፋሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያየሁትም ራእይ ከተማይቱን ለማጥፋት በመጣሁ ጊዜ እንዳየሁት ራእይ ነበረ፥ ራእዩም በኮቦር ወንዝ እንዳየሁት ራእይ ነበረ፥ እኔም በግምባሬ ተደፋሁ። |
የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ ብዛት ዋይ በል፥ እርሷንና የብርቱዎችን አሕዛብ ሴቶች ልጆች ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱ ጋር ወደ ታችኛው ምድር ጣላቸው።
የእስራኤልም አምላክ ክብር በላዩ ላይ አርፎ ከነበረበት ኪሩብ ተነሥቶ ወደ ቤቱ መግቢያ ሄዶ ነበር፥ በፍታ የለበሰውን በወገቡም የጸሐፊ ቀለም ቀንድ የያዘውን ሰው ጠራ።