ሕዝቅኤል 42:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውስጠኛውን ቤት ለክቶ ሲጨርስ ወደ ምሥራቅ በሚመለከት በር መንገድ አወጣኝ፥ ዙሪያውን ሁሉ ለካ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያለውን ስፍራ ለክቶ ከጨረሰ በኋላ፣ በምሥራቅ በር በኩል ወደ ውጩ አወጣኝ፤ በዙሪያው ያለውንም ስፍራ ሁሉ ለካ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያ ሰው የቤተ መቅደሱን ውስጣዊ ክፍሎች ለክቶ ከጨረሰ በኋላ፥ በምሥራቁ የቅጽር በር በኩል ወደ ውጪ አወጣኝ፤ ከዚያም በኋላ የውጪውን ክልል ለካ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ውስጠኛውንም ቤት ለክቶ በፈጸመ ጊዜ ወደ ምሥራቅ በሚመለከተው በር መንገድ አወጣኝ፤ እርሱንም ዙሪያውን ለካው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ውስጠኛውንም ቤት ለክቶ በፈጸመ ጊዜ ወደ ምሥራቅ በሚመለከት በር መንገድ አወጣኝ እርሱንም በዙሪያው ለካው። |
እነሆ፥ በቤቱ ውጭ በዙሪያው ቅጥር ነበረ፥ በሰውዬውም እጅ ያለው የመለኪያው ዘንግ ርዝመት አንድ ክንድ ከስንዝር የሆነ ስድስት ክንድ ነበረ፤ ቅጥሩንም ለካ፥ ስፋቱ አንድ ዘንግ፥ ቁመቱም አንድ ዘንግ ነበር።
ወደ ኋላውም ባለው በተለየው ስፍራ አንጻር የነበረውን የሕንጻውን ርዝመት በዚህና በዚያ የነበሩትን መተላለፊያዎች ጨምሮ ለካ፥ አንድ መቶ ክንድ ነበር። የቤተ መቅደሱ ውስጠኛው ክፍል፥ የአደባባዩ መተላለፊያዎች፥