Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 41:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ወደ ኋላውም ባለው በተለየው ስፍራ አንጻር የነበረውን የሕንጻውን ርዝመት በዚህና በዚያ የነበሩትን መተላለፊያዎች ጨምሮ ለካ፥ አንድ መቶ ክንድ ነበር። የቤተ መቅደሱ ውስጠኛው ክፍል፥ የአደባባዩ መተላለፊያዎች፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከዚያም ከቤተ መቅደሱ በስተጀርባ ከግቢው ትይዩ ያለውን ሕንጻ ለካ፤ ይህም በግራና በቀኝ ያሉትን መተላለፊያዎች የሚጨምር ሲሆን፣ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ ነበር። የውጩ መቅደስና የውስጡ መቅደስ ከአደባባዩ ትይዩ ያለው መተላለፊያ በረንዳ፣

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በሁለቱም በኩል ያሉትን መተላለፊያዎች ጨምሮ በምዕራብ በኩል ያለውን የሕንጻውን ርዝመት ሲለካው አንድ መቶ ክንድ ሆነ። የቤተ መቅደሱ መተላለፊያ፥ ቅዱሱ ስፍራና ወደ ውስጥ ዘልቆ የሚገኘው ቅድስተ ቅዱሳን፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ወደ​ኋ​ላ​ውም በአ​ለው በልዩ ስፍራ አን​ጻር የነ​በ​ረ​ውን የግ​ቢ​ውን ርዝ​መት፥ በዚ​ህና በዚያ ከነ​በ​ሩት ከግ​ን​ቦቹ ጋር አንድ መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ የው​ስ​ጡ​ንም መቅ​ደስ፥ የአ​ዳ​ራ​ሹ​ንም መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎች ለካ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ወደ ኋላውም ባለው በልዩ ስፍራ አንጻር የነበረውን የግቢውን ርዝመት በዚህና በዚያም ከነበሩት ከግንቦቹ ጋር አንድ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 41:15
13 Referencias Cruzadas  

በውስጠኛው አደባባይ በሀያው ክንድ ፊት ለፊት በውጭውም አደባባይ በወለሉ ፊት ለፊት በሦስት ደርብ በትይዩ የተሠራ መተላለፊያ ነበረ።


በሰሜን በኩል ወዳለው ወደ ውጪው አደባባይ አወጣኝ፥ በተለየው ስፍራ ፊት ለፊት፥ በሰሜን በኩል ባለው ህንጻ ፊት ለፊት ወዳለው ክፍል አገባኝ።


“የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በመንገዴ ብትሄድ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፥ በቤቴ ላይ ትፈርዳለህ፥ አደባባዮቼንም ትጠብቃለህ፤ እኔም በዚህ ስፍራ ከቆሙት ጋር ስፍራን እሰጥሃለሁ።”


ውስጠኛውን ቤት ለክቶ ሲጨርስ ወደ ምሥራቅ በሚመለከት በር መንገድ አወጣኝ፥ ዙሪያውን ሁሉ ለካ።


መተላለፊያው አሳጥሮአቸዋልና የላይኞቹ ክፍሎች ከመካከለኞቹና ከታችኞቹ ይልቅ አጫጭር ነበሩ።


ከበሩ በላይ እስከ ውስጠኛው ቤት ድረስ፥ በዙሪያውም የነበረው ግንብ ሁሉ ውጭውም ውስጡም ተለካ።


በባሕር መንገድ በኩል በተለየው ስፍራ አንጻር የነበረው ሕንጻ ስፋቱ ሰባ ክንድ ነበረ። የሕንጻው ግንብ ዙሪያ ውፍረቱ አምስት ክንድ ርዝመቱ ደግሞ ዘጠና ክንድ ነበረ።


ራስሽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ በላይሽ ነው፥ የራስሽም ጠጉር እንደ ሐምራዊ ሐር ነው፥ ንጉሡ በሹርባው ታስሮአል።


የቤታችን ሠረገላ የዝግባ ዛፍ ነው፥ የጣሪያችንም ማዋቀሪያ የጥድ ዛፍ ነው።


ቤቱንም ለካው፥ ርዝመቱ መቶ ክንድ ሆነ፥ የተለየው ስፍራ፥ ሕንጻውና ግንቡ አንድ መቶ ክንድ ሆነ።


የቤቱና በምሥራቅ በኩል የነበረው የተለየው ስፍራ ስፋት አንድ መቶ ክንድ ሆነ።


የቤቱ መግቢያዎች፥ ጠባቦቹ መስኮቶች፥ በዙሪያቸው የነበሩ ሦስት መተላለፊያዎች፥ የቤቱ መግቢያ ዙሪያውን ከመሬት ጀምሮ እስከ መስኮቶቹ ድረስ በእንጨት ተለብጦ ነበር፤ መስኮቶቹም የተሸፈኑ ነበሩ፤


በምሥራቅ በኩል ባለው አደባባይ ግንብ ርዝመት፥ በተለየው ስፍራና በሕንጻው ፊት ለፊት ክፍሎች ነበሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios