ሕዝቅኤል 32:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኃያላን ሰይፍ ብዙ ሕዝብህን እጥላለሁ፤ ከአሕዛብ ሁሉ ጨካኞች ናቸው፤ የግበጽንም ትዕቢት ያወድማሉ ብዛትዋም ሁሉ ይጠፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሕዝቦች ሁሉ እጅግ ጨካኝ በሆኑት፣ በኀያላን ሰዎች ሰይፍ፣ ያከማቸኸው ሰራዊት እንዲወድቅ አደርጋለሁ፤ የግብጽን ኵራት ያንኰታኵታሉ፤ የሰራዊቷም ብዛት ይጠፋል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዓለም ሕዝቦች በጣም ጨካኞች በሆኑት በኀያላን ሰይፍ፥ ብዛት ያለው ሕዝብህ ይወድቃል፤ እነርሱም የግብጽን ትዕቢት ያዋርዳሉ፤ ብዛት ያለው ሕዝብዋም ይጠፋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኀያላን ሰይፍ ኀይልህን እጥላለሁ፤ ሁሉ የአሕዛብ ጨካኞች ናቸው፤ የግብፅንም ትዕቢት ያጠፋሉ፤ ኀይልዋም ሁሉ ይደመሰሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኃያላን ሰይፍ የሕዝብህን ብዛት እጥላለሁ፥ ሁሉ የአሕዛብ ጨካኞች ናቸው፥ የግበጽንም ትዕቢት ያጠፋሉ ብዛትዋም ሁሉ ይጠፋል። |
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የግብጽን ምድር ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እሰጠዋለሁ፤ ብዛትዋን ያነሳል፥ ምርኮዋን ይማርካል፥ ብዝበዛዋንም ይበዘብዛል፤ ይህም ለሠራዊቱ ደመወዝ ይሆናል።
ባዕዳን፥ የሕዝቦች ጨካኞች የሆኑ፥ ቆርጠው ጣሉት፤ በተራሮች እና በሸለቆዎች ሁሉ ውስጥ ቅርጫፎቹ ወደቁ፥ ቅርንጫፎቹም በምድር ፈሳሾች ሁሉ ላይ ተሰባበሩ፥ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ ከጥላው ወጥተው ትተውት ሄዱ።
የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ ብዛት ዋይ በል፥ እርሷንና የብርቱዎችን አሕዛብ ሴቶች ልጆች ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱ ጋር ወደ ታችኛው ምድር ጣላቸው።