ሕዝቅኤል 31:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በቁመት ረዝመሃል፥ ጫፉን በቅርንጫፎች መካከል አድርጎአልና፥ ልቡም በቁመቱ ኰርቶአልና፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ጥቅጥቅ ባለው ቅጠል ላይ ጫፉን ከፍ በማድረግ ራሱን በማንጠራራቱ፣ በርዝማኔውም በመኵራራቱ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እንግዲህ አድጎ እስከ ደመናት በደረሰ መጠን፥ ትዕቢት በሚሰማው በዚያ ዛፍ ላይ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የማደርገው ይህ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቁመትህ ከፍ ከፍ ብሎአልና፥ ራስህም በደመናት መካከል ደርሶአልና፤ ትዕቢቱንም አየሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቁመትህ ከፍ ከፍ ብሎአልና፥ ራሱንም በደመናዎች መካከል አድርጎአልና፥ |
ጌታ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ የሚያደርገውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፤ እንዲህ ይላል የአሦርን ንጉሥ ስለ ልቡ ትዕቢትና ስለ ንቀት አመለካከቱ እቀጣዋለሁ፤
ወደ ጉድጓድ በሚወርዱ በሰው ልጆች መካከል ሁላቸው ለታችኛው ምድር ለሞት አልፈው ተሰጥተዋልና በውኃ አጠገብ ያሉ ዛፎች ሁሉ በቁመታቸው እንዳይረዝሙ፥ ራሳቸውንም በደመናዎች መካከል እንዳያደርጉ፥ ውኃንም የሚጠጡ ኃያላኖቻቸው ሁሉ በቁመታቸው እንዳይቆሙ።
በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ የምትኖር፥ ማደሪያህንም ከፍ ከፍ ያደረግህ፥ በልብህም፦ ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው? የምትል አንተ ሆይ፥ የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል።