ሕዝቅኤል 27:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሲዶናና የአርቫድ ነዋሪዎች ቀዛፊዎችሽ ነበሩ፤ ጢሮስ ሆይ፥ በአንቺ ውስጥ የነበሩት ባለሙያዎችሽ የመርከቦችሽ መሪዎች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀዛፊዎችሽ ከሲዶናና ከአራድ የመጡ ነበሩ፤ ጢሮስ ሆይ፤ የራስሽ ጠቢባን የመርከቦችሽ መሪዎች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀዛፊዎችሽ ሲዶናና አርዋድ ከተባሉ ከተሞች የመጡ ናቸው፤ ጢሮስ ሆይ! ባለሙያዎችሽ የመርከብ አዛዦችሽ ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለቆችሽ በሲዶና ይኖሩ ነበር፤ የአራድ ሰዎችም ቀዛፊዎችሽ ነበሩ፤ ጢሮስ ሆይ! ጥበበኞችሽ በአንቺ ዘንድ ነበሩ፤ የመርከቦችሽም መሪዎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሲዶናና የአራድ ሰዎች ቀዛፎችሽ ነበሩ፥ ጢሮስ ሆይ፥ ጥበበኞችሽ በአንቺ ዘንድ ነበሩ የመርከቦችሽም መሪዎች ነበሩ። |
ስለዚህ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት የሚቆርጡ ሰዎችን ወደ ሊባኖስ ላክልኝ፤ የእኔም ሰዎች ከእነርሱ ጋር አብረው እንዲሠሩ አደርጋለሁ፤ ለሰዎችህም አንተ የምትወስነውን ደመወዝ እከፍላለሁ፤ አንተ እንደምታውቀው የእኔ ሰዎች ስለ ዛፍ አቆራረጥ የአንተን ሰዎች ያኽል ዕውቀት የላቸውም።”
የአርቫድ ልጆችና ሠራዊቶችሽ በቅጥሮችሽ ላይ ዙሪያውን ነበሩ፥ ጋማዳውያንም በግንቦችሽ ውስጥ ነበሩ፤ ጋሻቸውንም በቅጥርሽ ዙሪያ ሰቀሉ፥ ውበትሽንም ፍጹም አደረጉ።
ጌታም በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ መቱአቸውም፥ ወደ ታላቂቱም ሲዶና፥ ወደ ማሴሮንም፥ በምሥራቅም በኩል ወዳለው ወደ ምጽጳ ሸለቆ አሳደዱአቸው፤ አንድም ሳያስቀሩ መቱአቸው።