Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 27:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 አለ​ቆ​ችሽ በሲ​ዶና ይኖሩ ነበር፤ የአ​ራድ ሰዎ​ችም ቀዛ​ፊ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ ጢሮስ ሆይ! ጥበ​በ​ኞ​ችሽ በአ​ንቺ ዘንድ ነበሩ፤ የመ​ር​ከ​ቦ​ች​ሽም መሪ​ዎች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ቀዛፊዎችሽ ከሲዶናና ከአራድ የመጡ ነበሩ፤ ጢሮስ ሆይ፤ የራስሽ ጠቢባን የመርከቦችሽ መሪዎች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የሲዶናና የአርቫድ ነዋሪዎች ቀዛፊዎችሽ ነበሩ፤ ጢሮስ ሆይ፥ በአንቺ ውስጥ የነበሩት ባለሙያዎችሽ የመርከቦችሽ መሪዎች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ቀዛፊዎችሽ ሲዶናና አርዋድ ከተባሉ ከተሞች የመጡ ናቸው፤ ጢሮስ ሆይ! ባለሙያዎችሽ የመርከብ አዛዦችሽ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የሲዶናና የአራድ ሰዎች ቀዛፎችሽ ነበሩ፥ ጢሮስ ሆይ፥ ጥበበኞችሽ በአንቺ ዘንድ ነበሩ የመርከቦችሽም መሪዎች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 27:8
13 Referencias Cruzadas  

ከነ​ዓ​ንም የበ​ኵር ልጁን ሲዶ​ንን፥ ኬጤ​ዎ​ንን፥


አራ​ዲ​ዎ​ንን፥ ሰማ​ር​ዮ​ንን፥ አማ​ቲ​ንን ወለደ። ከዚ​ህም በኋላ የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ነገድ ተበ​ተኑ።


“ዛብ​ሎን ጫማ​ውን አዝቦ ይኖ​ራል፤ እር​ሱም እንደ መር​ከ​ቦች ወደብ ይሆ​ናል፤ ዳር​ቻ​ውም እስከ ሲዶና ይሰ​ፋል።


አሁ​ንም ከወ​ገኔ እንደ ሲዶ​ና​ው​ያን እን​ጨት መቍ​ረጥ የሚ​ያ​ውቅ እን​ደ​ሌለ ታው​ቃ​ለ​ህና የዝ​ግባ ዛፍ ከሊ​ባ​ኖስ ይቈ​ር​ጡ​ልኝ ዘንድ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን እዘዝ፤ አገ​ል​ጋ​ዮቼም ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ጋር ይሁኑ፤ የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህ​ንም ዋጋ እንደ ተና​ገ​ር​ኸው ሁሉ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።”


ኪራ​ምም በእ​ነ​ዚያ መር​ከ​ቦች ከሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ጋር ባሕ​ሩን መቅ​ዘፍ የሚ​ያ​ውቁ መር​ከ​በ​ኞች አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ላከ።


አራ​ዴ​ዎ​ንን፥ ሰማ​ሬ​ዎ​ንን፥ አማ​ቲን ወለደ።


እንደ ሔማት አር​ፋድ፥ እንደ አር​ፋድ ሴፋ​ሩ​ሔም፥ እንደ ሴፋ​ሩ​ሔም ካሌና፥ እንደ ካሌ​ናም ደማ​ስቆ፥ እንደ ደማ​ስ​ቆም ሰማ​ርያ አይ​ደ​ለ​ች​ምን?


“ስለ ደማ​ስቆ፤ ክፉ ወሬ ሰም​ተ​ዋ​ልና ሐማ​ትና አር​ፋድ አፈሩ፤ ቀለ​ጡም፤ እንደ ባሕ​ርም ተነ​ዋ​ወጡ፤ ያር​ፉም ዘንድ አይ​ች​ሉም።


የአ​ራድ ልጆ​ችና ሠራ​ዊ​ቶ​ችሽ በቅ​ጥ​ሮ​ችሽ ላይ በዙ​ሪያ ነበሩ፤ ገማ​ዳ​ው​ያ​ንም በግ​ን​ቦ​ችሽ ውስጥ ነበሩ፤ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ው​ንም በዙ​ሪያ በቅ​ጥ​ርሽ ላይ አን​ጠ​ለ​ጠሉ፤ ውበ​ት​ሽ​ንም ፈጽ​መ​ዋል።


ከጩ​ኸ​ትሽ የተ​ነሣ የመ​ር​ከ​ብሽ መሪ​ዎች ፍር​ሀ​ትን ፈሩ።


የሰው ልጅ ሆይ! ፊት​ህን ወደ ሲዶና አቅ​ን​ተህ ትን​ቢት ተና​ገ​ር​ባት፤ እን​ዲ​ህም በል፦


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ መቱ​አ​ቸ​ውም፤ ወደ ታላ​ቂ​ቱም ሲዶና፥ ወደ ማሴ​ሮ​ንም፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ወዳ​ለው ወደ ሞሳሕ ሸለቆ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ ማን​ንም ሳያ​ስ​ቀሩ መቱ​አ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos