የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦
የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦
የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦
የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦
በቀንና በሌሊት በቅጥርዋ ይከብቡአታል፥ በደልና ሁከት በመካከልዋ ነው፥
ጽድቅ፥ ሕዝብን ከፍ ከፍ ታደርጋለች፥ ኃጢአት ግን ሕዝብን ታስነውራለች።
ታማኝ የነበረችው ከተማ እንዴት አመንዝራ እንደ ሆነች ተመልከቱ! ቀድሞ ፍትሕ የሞላባት፤ ጽድቅ የሰፈነባት ነበረች፤ አሁን ግን የነፍሰ ገዳዮች ማደሪያ ሆነች!
ሕመምህ የማይፈወስ ነውና ስለ ስብራትህ ለምን ትጮኻለህ? በደልህ ታላቅ ስለሆነ ኃጢአትህም ስለ በዛ፥ እነዚህን ነገሮች አድርጌብሃለሁ።
ለእሳት ማገዶ ትሆናለህ፥ ደምህም በምድር መካከል ይሆናል፥ ደግሞም አትታሰብም፤ እኔ ጌታ ተናግሬአለሁና።
አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ትፈርዳለህን? ደም በምታፈስስ ከተማ ላይ ትፈርዳለህን? ርኩሰትዋን ሁሉ አስታውቃት።