Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 30:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ሕመምህ የማይፈወስ ነውና ስለ ስብራትህ ለምን ትጮኻለህ? በደልህ ታላቅ ስለሆነ ኃጢአትህም ስለ በዛ፥ እነዚህን ነገሮች አድርጌብሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ፈውስ ለማይገኝለት ሕመምህ፣ ስለ ቍስልህ ለምን ትጮኻለህ? በደልህ ታላቅ፣ ኀጢአትህም ብዙ ስለ ሆነ፣ እነዚህን ሁሉ አድርጌብሃለሁና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ኃጢአታችሁ የበዛ ክፋታችሁም እጅግ ከፍ ያለ በመሆኑ ፈውስ ስለማይገኝላችሁ፥ ስለ ቊስላችሁ ሕመም አታጒረምርሙ፤ እኔ እንዲህ አድርጌ እቀጣችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ቍስ​ልህ የማ​ይ​ፈ​ወስ ሆኖ​አ​ልና ስለ ስብ​ራ​ትህ ለምን ትጮ​ኻ​ለህ? በደ​ልህ ታላቅ ስለ ሆነ፥ ኀጢ​አ​ት​ህም ስለ በዛ፥ ይህን አድ​ር​ጌ​ብ​ሃ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ሕመምህ የማይፈወስ ሆኖአልና ስለ ስብራትህ ለምን ትጮኻለህ? በደልህ ታላቅ ስለሆነ ኃጢአትህም ስለ በዛ፥ ይህን አድርጌብሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 30:15
45 Referencias Cruzadas  

በክፉ ሥራችንና በታላቁ በደላችን ከደረሰብን ነገር ሁሉ በኋላ፥ አንተ አምላካችን እንደ ኃጢአታችን ብዛት አልቀሠፍኸንም ነገር ግን ትሩፋንን ሰጠኸን።


ሕዝብንም ሆነ ሰውን በተመለከተ፥ ዝም ቢል የሚፈርድ ማን ነው? ፊቱንስ ቢሰውር የሚያየው ማን ነው?


ምንም እውነተኛ ብሆን እንደ ውሸተኛ ተቈጠርሁ፥ ምንም ባልበድል ቁስሌ የማይፈወስ ነው ብሏል።


በዓመፅ መንገዳቸው አላዋቂ ሆኑ፥ በጥፋታቸው ተጎሳቆሉ።


ከእግር ጥፍራችሁ እስከ ራስ ጠጉራችሁ ጤና የላችሁም፤ ቁስልና ዕባጭ እንዲሁም እዥ ብቻ ነው፤ አልታጠበም፤ አልታሰረም፤ በዘይትም አልለዘበም።


መሬቱን ቈፈረ፤ድንጋይንም ለቅሞ አወጣ፤ ምርጥ የሆነውንም ወይን ተከለበት። በመካከሉ መጠበቂያ ማማ ሠራ፤ የወይን መጭመቂያ ጉድጓድም አበጀ፤ ከዚያ መልካም ፍሬ ያፈራል ብሎ አሰበ፤ ነገር ግን ኮምጣጣ ፍሬ አፈራ።


ይሁዳ ሆይ! አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር እንዲሁ ናቸው፤ እንደ ኢየሩሳሌምም መንገዶች ቍጥር ለአሳፋሪ ነገር መሠዊያዎችን ሠርታችኋል፥ እነርሱም ለበዓል የምታጥኑባቸው መሠዊያዎች ናቸው።


ለምን ሕመሜ የማያቋርጥ ሆነ? ቁስሌስ የማይፈወስ ለምን ሆነ? ለምንስ፦ አልሽርም አለ? በውኑ እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃ ትሆንብኛለህን?


ክፋትሽ ይቀጣሻል ክህደትሽ ይገሥጽሻል፤ ጌታን አምላክሽን መተውሽ ምን ያኽል ክፉና መራራ ነገር እንደሆነ እወቂም፥ ተመልከቺም፤ እኔን መፍራት በአንቺ ውስጥ የለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


“ጌታ እንዲህ ይላል፦ ስብራትህ የማይፈወስ ቁስልህም የማይሽር ነው።


ውሽሞችህ ሁሉ ረስተውሃል አይፈልጉህምም፤ በደልህ ታላቅ ስለሆነ ኃጢአትህም ስለ በዛ፥ ጨካኝ ሰው እንደሚቀጣው ጠላትም እንደሚያቆስለው አቁስዬሃለሁና።


ስለዚህ የሚውጡህ ሁሉ ይዋጣሉ፥ ጠላቶችህም ሁሉ አንድም ሳይቀሩ ይማረካሉ፤ የዘረፉህም ይዘረፋሉ፥ የበዘበዙህንም ሁሉ ለመበዝበዝ አሳልፌ እሰጣለሁ።


‘ማንም የማይሻት ጽዮን!’ ‘የተጣለች’ ብለው ጠርተውሻልና እኔ ጤናሽን እመልስልሻለሁ ቁስልሽንም እፈውሳለሁ፥ ይላል ጌታ።


ድንግሊቱ የግብጽ ልጅ ሆይ! ወደ ገለዓድ ውጪ የሚቀባንም መድኃኒት ውሰጂ፤ ብዙ መድኃኒቶችን የተጠቀምሺው በከንቱ ነው፤ ለአንቺ መዳኛ የለሽም።


“ከታናናሾቻቸው ጀምሮ እስከ ታላላቆቻቸ ድረስ ሁሉም በግፍ ለሚገኝ ጥቅም ስስታም ናቸውና፥ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ተንኰልን ይፈጽማሉ።


ሄ። ስለ ኃጢአትዋ ብዛት እግዚአብሔር አስጨንቆአታልና አስጨናቂዎችዋ ራስ ሆኑ ጠላቶችዋም ተከናወነላቸው፥ ሕፃናቶችዋ በአስጨናቂዎች ፊት ተማርከዋል።


ሜም። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ አጽናናሽ ዘንድ በምን አስተካክልሻለሁ? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፥ የሚፈውስሽ ማን ነው?


ሕያው ሰው የሚያጉረመርም፥ ሰው ስለ ኃጢአቱ ቅጣት የሚያጉረመርም ስለ ምንድነው?


ሜም። የጻድቃንን ደም በውስጥዋ ስላፈሰሱ ስለ ነቢዮችዋ ኃጢአትና ስለ ካህናቶች በደል ነው።


ቁስልዋ የማይፈወስ ነውና፤ ወደ ይሁዳ መጥቷል፥ ወደ ሕዝቤ በር ወደ ኢየሩሳሌምም ደርሶአል።


በእርሱ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና፥ ጉዳዬን እስኪምዋገትልኝ ድረስ፥ ፍርድን እስኪያደርግልኝ ድረስ የጌታን ቁጣ እታገሣለሁ። ወደ ብርሃን ያወጣኛል፥ ጽድቁንም አያለሁ።


ስብራትህን የሚያሽል የለም፥ ቁስልህ የከፋ ነው፤ ወሬህን የሰሙ ሁሉ እጃቸውን በአንተ ላይ ያጨበጭባሉ፤ የማያቋርጥ ክፋትህ ያላለፈበት ማን ነውና?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos