ሰዎች ከሩቅ የሚመጡት ስለ ታላቁ ስምህ፥ ስለ ጠንካራዪቱ እጅህ፥ ስለ ተዘረጋችው ክንድህ ሰምተው ነውና፤ እንግዳው መጥቶ ወደዚህ ቤተ መቅደስ ቢጸልይ፥
ሕዝቅኤል 20:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ሕያው ነኝና በበረታች እጅና በተዘረጋች ክንድ በፈሰሰችም መዓት እነግሥባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሕያውነቴ እምላለሁ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ በብርቱ ክንድና በተዘረጋች እጅ መዓትንም በማፍሰስ በላያችሁ እነግሣለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ ሕያው እንደ መሆኔ በእርግጥ በሥልጣኔ፥ በሙሉ ኀይሌና በቊጣዬ በእናንተ ላይ እነግሣለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እኔ ሕያው ነኝ! በበረታች እጅና በተዘረጋች ክንድ፥ በፈሰሰችም መዓት እነግሥባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ሕያው ነኝና በበረታች እጅና በተዘረጋች ክንድ በፈሰሰችም መዓት እነግሥባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። |
ሰዎች ከሩቅ የሚመጡት ስለ ታላቁ ስምህ፥ ስለ ጠንካራዪቱ እጅህ፥ ስለ ተዘረጋችው ክንድህ ሰምተው ነውና፤ እንግዳው መጥቶ ወደዚህ ቤተ መቅደስ ቢጸልይ፥
ስለዚህም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፦ ‘እኔ ጌታ ነኝ፥ ከግብፃውያን ጭቆና አወጣችኋለሁ፥ ከተገዥነታችሁም አላቅቃችኋለሁ፤ በተዘረጋች ክንድ በታላቅ የፍርድ ሥራም አድናችኋለሁ፤
ግብጻውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ ጌታ እጁን በሚዘረጋ ጊዜ፥ ረጂው ይሰናከላል ተረጂውም ይወድቃል፥ ሁሉም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ተናግሮአልና፦ ቁጣዬና መዓቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ላይ እንደ ወረደ፥ እንዲሁ ወደ ግብጽ በገባችሁ ጊዜ መዓቴ ይወርድባችኋል፤ እናንተም ለጥላቻና ለመሣቀቂያ ለመረገሚያና ለመሰደቢያ ትሆናላችሁ፥ ይህንም ስፍራ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩትም።
አለቆችዋንና ጥበበኞችዋንም፥ ገዢዎችዋንና ሹማምቶችዋን ኃያላኖችዋንም አሰክራለሁ፥ ለዘለዓለምም አንቀላፍተው አይነቁም፥ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ የተባለው ንጉሥ።
ዳሌጥ። ቀስቱን እንደ ጠላት ገተረ፥ እንደ አስጨናቂ ቀኝ እጁን አጸና፥ ለዓይንም የሚያምረውን ሁሉ ገደለ፥ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳን መዓቱን እንደ እሳት አፈሰሰ።
እጄንም በእነሱ ላይ እዘረጋለሁ፥ በሚኖሩበትም ስፍራ ሁሉ ምድሪቱን ከዲብላ ምድረ በዳ ይልቅ ውድማና በረሃ አደርጋታለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።
እርሷም፦ “ውሽሞቼ ለእኔ የሰጡኝ ዋጋዬ ይህ ነው” ያለችውን ወይንዋንና በለስዋን አጠፋለሁ፤ ዱርም አደርገዋለሁ፥ የምድረ በዳም አራዊት ይበሉታል።