ንጉሥ ኒካዑ የኢዮስያስ ልጅ ኤልያቄም በአባቱ በኢዮስያስ እግር ተተክቶ በይሁዳ እንዲነግሥ አደረገ፤ ስሙንም በመለወጥ ኢዮአቄም ብሎ ጠራው፤ ኢዮአሐዝም በንጉሥ ነኮ ተማርኮ ወደ ግብጽ ተወሰደ፤ በዚያም ሞተ።
ሕዝቅኤል 19:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከግልገሎችዋም አንዱን አሳደገችው፥ እርሱም ደቦል አንበሳ ሆነ፥ አደንም ተማረ፥ ሰዎችን በላ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከግልገሎቿ መካከል አንዱን አሳደገችው፤ እርሱም ብርቱ አንበሳ ሆነ። ግዳይ መንጠቅን ተማረ፤ ሰዎችንም በላ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከግልገሎችዋ አንዱን ተንከባክባ አሳደገችው እርሱም ደቦል ሆነ፤ አደንንም ተማረ፤ ሰውንም መብላት ጀመረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከግልገሎችዋም አንዱን አወጣች፤ እርሱም ደቦል አንበሳ ሆነ፤ ንጥቂያንም ተማረ፤ ሰዎችንም ነጥቆ በላ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከግልገሎችዋም አንዱን አወጣች እርሱም ደቦል አንበሳ ሆነ፥ ንጥቂያንም ተማረ፥ ሰዎችንም በላ። |
ንጉሥ ኒካዑ የኢዮስያስ ልጅ ኤልያቄም በአባቱ በኢዮስያስ እግር ተተክቶ በይሁዳ እንዲነግሥ አደረገ፤ ስሙንም በመለወጥ ኢዮአቄም ብሎ ጠራው፤ ኢዮአሐዝም በንጉሥ ነኮ ተማርኮ ወደ ግብጽ ተወሰደ፤ በዚያም ሞተ።
እንዲህም በል፦ እናትህ በአንበሶች መካከል እንዴት ያለች እንስት አንበሳ ነበረች! በደቦል አንበሶች መካከል ተቀምጣ ግልገሎችዋን አሳደገች።
በውስጧ ያሉ ነቢያት እንደሚጮኽና የገደለውን እንደሚበላ አንበሳ ናቸው፤ ነፍሶችን በልተዋል፥ ሀብትንና የከበሩ ነገሮችን ወስደዋል፤ በውስጧም ብዙዎችን መበለቶች አድርገዋል።
የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አውርድ፥ እንዲህም በለው፦ በሕዝቦች መካከል አንበሳ መሰልህ፥ እንደ ባሕር አውሬ ነበርህ፤ በወንዞችህም ገንፍለህ ወጥተሃል፥ ውኃውንም በእግርህ አደፍርሰሃል፥ ወንዞችህንም አሳድፈሃል።