በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ ለዘለዓለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ፥ አምላክም እሆናቸዋለሁ።”
ሕዝቅኤል 11:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም በትእዛዜ እንዲሄዱ፥ ፍርዴንም እንዲጠብቁና እንዲፈጽሙ ነው፤ ስለዚህ እነርሱ ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ትእዛዜን ይፈጽማሉ፤ ሕጌን ይጠብቃሉ። እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ሕጌን ይፈጽማሉ፤ ሥርዓቴንም ሁሉ ያከብራሉ፤ እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በትእዛዜም ይሄዱ ዘንድ፥ ፍርዴንም ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ እነርሱ ሕዝብ ይሆኑኛል፥ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ። |
በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ ለዘለዓለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ፥ አምላክም እሆናቸዋለሁ።”
ይህንንም ከግብጽ አገር ከብረት ምድጃ ባወጣኋቸው ቀን ለአባቶቻችሁ ያዘዝኩት ቃላት ነው፤ አልሁም፦ ድምፄን ስሙ፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ አድርጉ፤ እንዲሁም እናንተ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ።
“የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እንደዚህ እንደ መልካሙ በለስ፥ እንዲሁ ከዚህ ስፍራ ወደ ከለዳውያን ምድር የላክሁትን የይሁዳን ምርኮ በበጐነት እመለከተዋለሁ።
ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የማደርገው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።
እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ፤ በትእዛዜ አልሄዳችሁምና፥ ሕጌንም አልፈጸማችሁምና፥ ነገር ግን በዙሪያችሁ እንደሚኖሩት እንደ አሕዛብ ሕግ አድርጋችኋል።
ይኸውም የእስራኤል ቤት ደግመው ከእኔ ርቀው እንዳይጠፉ፥ በመተላለፋቸውም ሁሉ እንዳይረክሱ ነው፥ እነርሱ ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
በጣዖቶቻቸው፥ በአጸያፊ ነገሮቻቸውና በመተላለፋቸው ሁሉ ዳግመኛ አይረክሱም፤ ኃጢአት ከሠሩባቸው መኖሪያ ቤቶቻቸው ሁሉ አድናቸዋለሁ፥ አነጻቸዋለሁም፤ እነርሱ ለእኔ ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።
በሠሩት ሥራ ሁሉ የሚያፍሩ ከሆነ፥ የቤቱን ንድፉንና አሠራሩን፥ መውጫውንና መግቢያውን፥ አጠቃላይ ንድፉን፥ ሥርዓቱን ሁሉ፥ ንድፉን ሁሉ፥ ሕጉን ሁሉ አሳውቃቸው፤ ንድፉን ሁሉና ሥርዓቱን ሁሉ እንዲያዩትና እንዲያደርጉትም በፊታቸው ጻፈው።
አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አስገባለሁ፤ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፤ እኔም፦ “ይህ ሕዝቤ ነው” እላለሁ፥ እርሱም፦ “ጌታ አምላኬ ነው” ይላል።
ጌታ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ እንድትወደው፥ በሕይወትም እንድትኖር፥ አምላክህ ጌታ የአንተንና የዘርህን ልብ ይገርዛል።
አሁን ግን የሚበልጠውን ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና አምላካቸው ተብሎ ለመጠራት በእነርሱ አያፍርም።
ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው፥ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆንላቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑልኛል።