ሕዝቅኤል 37:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 በጣዖቶቻቸው፥ በአጸያፊ ነገሮቻቸውና በመተላለፋቸው ሁሉ ዳግመኛ አይረክሱም፤ ኃጢአት ከሠሩባቸው መኖሪያ ቤቶቻቸው ሁሉ አድናቸዋለሁ፥ አነጻቸዋለሁም፤ እነርሱ ለእኔ ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 በጣዖቶቻቸው፣ በአስጸያፊ ምስሎቻቸው ወይም በማንኛውም ኀጢአት ራሳቸውን አያረክሱም፤ ነገር ግን እኔን በመተው ከሠሩት ኀጢአት ሁሉ አድናቸዋለሁ፤ አነጻቸዋለሁም። እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ዳግመኛ በጣዖቶቻቸው፥ በአጸያፊ ነገሮቻቸው፥ ወይም በሌሎች ኃጢአቶቻቸው ራሳቸውን አያረክሱም፤ ከወደቁበት ክሕደት አውጥቼ አነጻቸዋለሁ። በዚያን ጊዜ እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 ከዚያ ወዲያም በጣዖቶቻቸውና በርኵሰታቸው፥ በመተላለፋቸውም ሁሉ አይረክሱም፤ ኀጢአትም ከሠሩባት ዐመፅ ሁሉ አድናቸዋለሁ፤ አነጻቸውማለሁ፤ ሕዝብም ይሆኑኛል፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 ከዚያ ወዲያም በጣዖቶቻቸውና በርኵሰታቸው በመተላለፋቸውም ሁሉ አይረክሱም፥ ኃጢአትም ከሠሩባት ዓመፅ ሁሉ አድናቸዋለሁ አነጻቸውማለሁ፥ ሕዝብም ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ። Ver Capítulo |