ሕዝቅኤል 1:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግሮቻቸውም ቀጥ ያሉ እግሮች ነበሩ፥ የእግሮቻቸውም ኮቴ እንደ ጥጃ እግር ኮቴ ነበረ፥ እንደ ተወለወለ ናስም ያንጸባርቅ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግራቸው ቀጥ ያለ ነበር፤ ኰቴያቸውም እንደ ጥጃ ኰቴ ያለ ሲሆን፣ እንደ ተወለወለ ናስም ያብለጨልጭ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግራቸው ቀጥ ያለ ሲሆን፥ ውስጥ እግራቸው እንደ ኰርማ ሰኮና ነበር፤ መልካቸውም እንደ ተወለወለ ነሐስ ያበራ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግሮቻቸውም ቀጥ ያሉ ነበሩ፤ የእግራቸው ሰኰና እንደ ላም እግር ሰኰና ነበረ፤ እንደ ተወለወለ ናስም ይብለጨለጭ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግሮቻቸውም ቀጥ ያሉ እግሮች ነበሩ፥ የእግራቸውም ኮቴ እንደ ጥጃ እግር ኮቴ ነበረ፥ እንደ ተወለወለ ናስም ይብለጨለጭ ነበር። |
የሕያዋኑም መልክ የሚነድድ የእሳት ፍም ይመስል ነበር፥ በሕያዋኑም መካከል የሚነድድ ችቦ የሚመስል ወዲህና ወዲያ ይዘዋወር ነበር፥ እሳቱም ብርሃን ነበረው፥ ከእሳቱም መብረቅ ይወጣ ነበር።
ወደዚያም አመጣኝ፥ እነሆ፥ መልኩ ናስ የመሰለ አንድ ሰው በዚያ ነበረ፥ በእጁም የተልባ እግር ገመድና የመለኪያ ዘንግ ይዞ ነበረ፤ እርሱም በበሩ አጠገብ ቆሞ ነበር።