ሕዝቅኤል 1:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 የሕያዋኑም መልክ የሚነድድ የእሳት ፍም ይመስል ነበር፥ በሕያዋኑም መካከል የሚነድድ ችቦ የሚመስል ወዲህና ወዲያ ይዘዋወር ነበር፥ እሳቱም ብርሃን ነበረው፥ ከእሳቱም መብረቅ ይወጣ ነበር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 የሕያዋን ፍጡራኑ መልክም እንደሚነድ የከሰል ፍምና የተቀጣጠለ ችቦ ይመስል ነበር፤ በፍጡራኑ መካከል እሳት ወዲያ ወዲህ ይንቀሳቀስ ነበር፤ ብርሃኑም ደማቅ ነበር፤ ከእሳቱም ውስጥ መብረቅ ይወጣ ነበር። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 በሕያዋን ፍጥረቶቹ መካከል እንደሚነድ ከሰል እሳት የሚመስል ነገር ነበር፤ እርሱም በፍጥረቶቹ መካከል ወዲያና ወዲህ የሚንቀሳቀስ ችቦ ይመስል ነበር፤ እሳቱ ብሩህ ነበር፤ መብረቅም ከዚያ ይወጣ ነበር። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 በእንስሶቹም መካከል እንደሚነድድ የእሳት ፍም ያለ አምሳያ ነበረ፤ በእንስሶቹ መካከል ወዲህና ወዲያ የሚሄድ እንደ ፋና ያለ አምሳያ ነበረ፤ ለእሳቱም ፀዳል ነበረው፤ ከእሳቱም መብረቅ ይወጣ ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 በእንስሶቹ መካከል እንደሚነድድ የእሳት ፍም ያለ ምስያ ነበረ፥ በእንስሶች መካከል ወዲህና ወዲያ የሚሄድ እንደ ፋና ያለ ምስያ ነበረ፥ ለእሳቱም ፀዳል ነበረው፥ ከእሳቱም መብረቅ ይወጣ ነበር። Ver Capítulo |