ይህም የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር ሶርያውያንን በፈረሶችና በሠረገሎች የታጀበ የብዙ ሠራዊት ግሥጋሤ የሚመስል ድምፅ አሰምቶአቸው ስለ ነበር ነው፤ ይኸውም ሶርያውያን እንዳሰቡት የእስራኤል ንጉሥ የሒታውያንና የግብጽ ነገሥታትን ከነሠራዊቶቻቸው ቀጥሮ አደጋ ሊጥልባቸው የመጣ መስሎአቸው ነበር።
ሕዝቅኤል 1:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሲሄዱም የክንፎቻቸውን ድምፅ እንደ ብዙ ውኆች ድምፅ፥ እንደ ሁሉን የሚችል አምላክ ድምፅ፥ እንደ ማዕበል ድምፅ፥ እንደ የታላቅ ሠራዊት ድምፅ ሆኖ ሰማሁ፤ ሲቆሙም ክንፎቻቸውን ዝቅ ያደርጉ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍጡራኑ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ የክንፎቻቸውን ድምፅ ሰማሁ፤ ድምፁም እንደሚጐርፍ ውሃ ጩኸት፣ ሁሉን ቻይ አምላክ ድምፅና እንደ ሰራዊት ውካታ ነበር። መንቀሳቀሳቸውን ሲያቆሙም ክንፎቻቸውን ዝቅ ያደርጉ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሚበርሩበትም ጊዜ ክንፎቻቸው ሲጋጩ ሰማሁ፤ ድምፁም የባሕር ማዕበል ጩኸትና የታላቅ ሠራዊት ሁካታ፥ እንዲሁም የሁሉን ቻዩን የእግዚአብሔርን ድምፅ ይመስል ነበር፤ መብረራቸውን ባቆሙ ጊዜ ክንፎቻቸውን ያጥፉ ነበር፤ በዚያን ጊዜ ከራሳቸው በላይ ካለው ጠፈር ድምፅ ተሰማ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሲሄዱም የክንፎቻቸው ድምፅ እንደ ብዙ ውኃ ድምፅ፥ ሁሉን እንደሚችል የአምላክም ድምፅ፥ እንደ ታላቅ ሠራዊትም ድምፅ ሆኖ ሰማሁ፤ ሲቆሙም ክንፎቻቸውን ይሰበስቡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሲሄዱም የክንፎቻቸውን ድምፅ እንደ ብዙ ውኃ ድምፅ፥ እንደ ሁሉን የሚችል የአምላክም ድምፅ፥ እንደ ታላቅም ሠራዊት ድምፅ ሆኖ ሰማሁ፥ ሲቆሙም ክንፎቻቸውን ዝቅ ያደርጉ ነበር። |
ይህም የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር ሶርያውያንን በፈረሶችና በሠረገሎች የታጀበ የብዙ ሠራዊት ግሥጋሤ የሚመስል ድምፅ አሰምቶአቸው ስለ ነበር ነው፤ ይኸውም ሶርያውያን እንዳሰቡት የእስራኤል ንጉሥ የሒታውያንና የግብጽ ነገሥታትን ከነሠራዊቶቻቸው ቀጥሮ አደጋ ሊጥልባቸው የመጣ መስሎአቸው ነበር።
ይህም የሕያዋኑ ክንፎች እርስ በእርሳቸው ሲማቱ የሚወጣው ድምፅ፥ በአጠገባቸውም የነበሩት የመንኰራኵሮች ድምፅ ነበር፥ እርሱም ታላቅ የሚያጉረመርም ድምፅ ነበር።
የብዙ ሕዝብም ድምፅ፥ የብዙ ውሃዎችም ድምፅ፥ የብርቱም ነጐድጓድም ድምፅ የሚመስል ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።