La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 9:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ገብሱና ተልባው ተመታ፤ ገብሱ ገና እሸት ተልባውም እንቡጥ ስለ ነበረ ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ተልባው አብቦ፣ ገብሱም ፍሬ ይዞ ስለ ነበር፣ ተልባውና ገብሱ ከጥቅም ውጭ ሆኑ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ገብስ ገና እሸት፥ ተልባውም ገና በማበብ ላይ ስለ ነበር አንድም ሳይቀር በሙሉ ተበላሸ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ተል​ባ​ውና ገብሱ ተመታ፤ ገብሱ አሽቶ፥ ተል​ባ​ውም አፍ​ርቶ ነበ​ርና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ገብሱ አሽቶ ተልባውም ኣፍርቶ ነበርና ተልባና ገብሱ ተመታ።

Ver Capítulo



ዘፀአት 9:31
6 Referencias Cruzadas  

ከዚያም ለገባዖናውያን አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ገድለው በኰረብታው ላይ በጌታ ፊት ሰቀሏቸው። ሰባቱም በአንድነት ሞቱ፤ የተገደሉትም እህል በሚታጨድበት ወራት በገብሱ መከር መጀመሪያ ነበር።


ስንዴውና አጃው ግን ጊዜው ገና ነበርና አልተመታም።


“በዋግና በአረማሞ መታኋችሁ፤ የአታክልቶቻችሁንም ብዛት ወይኖቻችሁንም በለሶቻችሁንም ወይራዎቻችሁንም ተምች በላው፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥” ይላል ጌታ።


የበለስ ዛፍ ባታብብም፥ በወይን ተክሎች ላይ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ምርት ቢቋረጥ፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ከብቶችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥


ስለዚህ ናዖሚ፥ ከሞአባዊት ምራትዋ ከሩት ጋር፥ ከሞዓብ አገር ተመለሰች። የገብስም መከር መሰብሰቢያ ጅማሬ ላይ ቤተልሔም መጡ።


ሩትም የገብሱና የስንዴው መከር እስኪጨረስ ድረስ ልትቃርም የቦዔዝ ሠራተኞች አጠገብ እየቃረመች ቈየች፥ ከአማቷም ሳትለይ አብራ ተቀመጠች።