ዘፀአት 9:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም ልኮ ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “በዚህ ጊዜ ኃጢአትን ሰርቻለሁ፤ ጌታ ጻድቅ ነው፥ እኔና ሕዝቤም በደለኞች ነን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ፈርዖን ሙሴንና አሮንን አስጠራ፤ እንዲህም አላቸው፤ “አሁንስ በድያለሁ፤ እግዚአብሔር ትክክል ነው፤ እኔና ሕዝቤ ግን ስተናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “አሁንስ በድዬአለሁ፤ እግዚአብሔር እውነተኛ ነው፤ እኔና ሕዝቤ ግን በደለኞች ነን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ልኮ ሙሴንና አሮንን ጠራ፤ “አሁንም በደልሁ፤ እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ እኔና ሕዝቤ ግን ኀጢአተኞች ነን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ልኮ ሙሴንና አሮንን ጠራ፤ “በዚህ ጊዜ በደልሁ፤ እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ እኔና ሕዝቤም ኃጢያተኞች ነን። |
ሙሴም፦ “እነሆ እኔ ከአንተ ዘንድ እወጣለሁ፥ የዝንቡም መንጋ ከፈርዖን፥ ከአገልጋዮቹና ከሕዝቡ ነገ እንዲሄዱ ወደ ጌታ እጸልያለሁ፤ ነገር ግን ለጌታ ይሠዋ ዘንድ ሕዝቡን እንዳይለቅቅ ፈርዖን እንደገና አያታልለን” አለ።
ጻዴ። በአፉ ነገር ላይ ዓመጽ አድርጌአለሁና እግዚአብሔር ጻድቅ ነው። እናንተ አሕዛብ ሁሉ፥ እባካችሁ፥ ስሙ መከራዬንም ተመልከቱ፥ ደናግሎቼና ጐበዛዝቴ ተማርከው ሄዱ።
ሕዝቡም ወደ ሙሴ መጥተው እንዲህ አሉት፦ “በጌታና በአንተ ላይ ስለ ተናገርን ኃጢአት ሠርተናል፤ እባቦቹን ከእኛ እንዲያርቅልን ወደ ጌታ ጸልይልን።” ሙሴም ስለ ሕዝቡ ጸለየ።
በለዓምም የጌታን መልአክ እንዲህ አለው፦ “ኃጢአትን ሠርቻለሁ፤ አንተ በመንገድ ላይ ልትቃወመኝ መቆምክን አላወቅሁም፤ እንግዲህም ይህ አሁን በፊትህ ክፉ የሆነ ነገር ቢሆን እመለሳለሁ።”
ነገር ግን አፍ ሁሉ እንዲዘጋና ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ ሥር እንዲሆን፤ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንደሚናገር እናውቃለን፤
ሳኦልም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ኃጢአት ሠርቼአለሁ፤ የጌታን ትእዛዝና የአንተን ቃል አልጠበቅሁም፤ ሕዝቡን በመፍራት የፈለጉትን ሁሉ አደረግሁ፤
ሳኦልም መልሶ፥ “ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ ነገር ግን በሕዝቤ አለቆች ፊትና በእስራኤል ፊት አክብረኝ፤ ለአምላክህ ለጌታ እሰግድ ዘንድ እባክህ አብረኸኝ ተመለስ” አለው።
ሳኦልም፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! በእርግጥ ተሳስቻለሁ፤ ተመለስ፤ ዛሬ ነፍሴ በፊትህ ስለከበረች ከእንግዲህ ወዲያ አልጐዳህም፤ ይሄው፥ የሞኝ ሥራ ሠራሁ፤ አብዝቼም ተሳሳትኩ” አለ።