ዘፀአት 6:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአሮንም ልጅ ኤልዓዛር ከፑቲኤል ልጆች አንዷን ሚስት አገባ፥ እርሷም ፒንሐስን ወለደችለት። እነዚህ እንደ ወገኖቻቸው የሌዋውያን አባቶች አለቆች ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአሮን ልጅ አልዓዛር ከፉትኤል ሴት ልጆች አንዷን አገባ፤ እርሷም ፊንሐስን ወለደችለት። እነዚህ እንደየነገዳቸው የሌዋውያን ጐሣዎች አለቆች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአሮን ልጅ አልዓዛር የፑቲኤልን ልጅ አገባ፤ እርስዋም ፊኒሐስን ወለደችለት፤ እነዚህ ሁሉ የሌዊ የነገድ አባቶችና አለቆች ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሮንም ልጅ አልዓዛር ከፋትኤል ልጆች ሚስትን አገባ፤ እርስዋም ፊንሐስን ወለደችለት። እነዚህም በየወገኖቻቸው የሌዋውያን አባቶች አለቆች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሮንም ልጅ አልዓዛር ከፉትኤል ልጆች ሚስት አገባ፤ እርስዋም ፊንሐስን ወለደችለት። እነዚህ እንደ ወገኖቻቸው የሌዋውያን አባቶች አለቆች ናቸው። |
ከሌዋውያንም በየወገናቸው የተቈጠሩት እነዚህ ናቸው፤ ከጌድሶን የጌድሶናውያን ወገን፥ ከቀዓት የቀዓታውያን ወገን፥ ከሜራሪ የሜራራውያን ወገን።
ሙሴም ከየነገዱ አንድ አንድ ሺህ ወደ ጦርነት ላከ፤ እነርሱንና የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ወደ ጦርነት ላካቸው፤ የመቅደሱንም ዕቃ የሚነፋውንም የማስጠንቀቂያ መለከት በእጁ ሰጠው።
የእስራኤልም ልጆች በገለዓድ ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ጋድ ልጆች ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ላኩ።
የአሮን ልጅ፤ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስም በፊቱ ይቆም ነበር። እስራኤላውያንም፥ “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን እንደገና ሄደን ጦርነት እንግጠማቸው ወይስ ይቅር?” ሲሉ ጠየቁ። ጌታም፥ “ሂዱ፤ በነገው ዕለት በእጃችሁ እሳልፌ እሰጣችኋለሁ” አላቸው።