ሰሎሞን በነገሠ በዐሥራ አንደኛ ዓመቱ፥ ቡል ተብሎ በሚጠራው በስምንተኛው ወር ላይ የቤተ መቅደሱ ሥራ ልክ በታቀደው መሠረት ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ፤ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ለመሥራት የፈጀበት ጊዜ ሰባት ዓመት ነበር።
ዘፀአት 39:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ ልክ እንደዛው አድርገው ሠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን ልክ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ሥራውን ሁሉ አከናወኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን ሥራውን ሁሉ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሠሩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ ሁሉ እንዲሁ የእስራኤል ልጆች ሥራውን ሁሉ ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ ሁሉ እንዲሁ የእስራኤል ልጆች ሥራውን ሁሉ ሠሩ። |
ሰሎሞን በነገሠ በዐሥራ አንደኛ ዓመቱ፥ ቡል ተብሎ በሚጠራው በስምንተኛው ወር ላይ የቤተ መቅደሱ ሥራ ልክ በታቀደው መሠረት ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ፤ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ለመሥራት የፈጀበት ጊዜ ሰባት ዓመት ነበር።
የመገናኛው ድንኳን የማደሪያው ሥራ ሁሉ ተጠናቀቀ። የእስራኤልም ልጆች ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ልክ እንደዛው አድርገው ሠሩ፤ እንዲሁ አደረጉ።
በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነትም እንዲያገለግሉበት የተቀደሱትን የካህኑን የአሮንን ልብሶችና የልጆቹን ልብሶች አመጡ።
ደመናውም ሁለት ቀን ወይም አንድ ወር ወይም ረጅም ጊዜ ቆይቶ በማደሪያው ላይ ቢቀመጥ የእስራኤል ልጆች በሰፈራቸው ይቀመጡ ነበር፥ አይጓዙምም ነበር፤ ነገር ግን በተነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር።
የእውነትን ቃል በትክክለኛው መንገድ እየገለጥህ፥ የሚያፍርበት ነገር እንደሌለው ሠራተኛ፥ ለእግዚአብሔር ብቁ ተደርገህ ራስህን ለማቅረብ የተቻለህን ሁሉ ጣር።