ዘፀአት 39:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአራተኛውም ረድፍ ቢረሌ፥ መረግድና ኢያስጲድ በወርቅ ፈርጥ ተደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአራተኛውም ረድፍ ቢረሌ፣ መረግድና ኢያሰጲድ ነበረ፤ በወርቅ ፈርጥ ላይ ተደርገው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአራተኛው ረድፍ ቢረሌ፥ መረግድና ኢያስጲድ፤ እነዚህ ሁሉ በወርቅ ፈርጥ ላይ የተቀመጡ ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአራተኛውም ተራ ወርቃማ ድንጋይ፥ ቢረሌ፥ ሶም፤ ዙሪያውም በወርቅ ፈርጥ ተደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአራተኛውም ተራ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያስጲድ በወርቅ ፈርጥ ተደረጉ። |
እኔም እንደ ጉልበቴ ሁሉ ለአምላኬ ቤት ለወርቁ ዕቃ ወርቁን፥ ለብሩም ዕቃ ብሩን፥ ለናሱም ዕቃ ናሱን፥ ለብረቱም ዕቃ ብረቱን፥ ለእንጨቱም ዕቃ እንጨቱን፥ ደግሞ መረግድንና በፈርጥ የሚገባ ድንጋይን፥ የሚለጠፍ ድንጋይን፥ ልዩ ልዩ መልክ ያለውንም ድንጋይ፥ የከበረውንም ድንጋይ ከየዓይነቱ፥ ብዙም እብነ በረድ አዘጋጅቻለሁ።
የዕንቁዎቹም ድንጋዮች እንደ ዐሥራ ሁለቱ እንደ እስራኤል ልጆች ስሞች ነበሩ፥ በየስማቸውም ማተሚያ እንደሚቀረጽ ተቀረጹ፥ ስለ ዐሥራ ሁለቱም ነገዶች ነበሩ።
የመንኰራኵሩም መልክና አሠራር የቢረሌ መልክ ይመስል ነበር፥ የአራቱም መልክ አንድ ዓይነት ነበር፥ መልካቸውና አሠራራቸው በመንኰራኵር መካከል ያለ መንኰራኵር ይመስል ነበር።
አምስተኛው ሰርዶንክስ፥ ስድስተኛው ሰርድዮን፥ ሰባተኛው ክርስቲሎቤ፥ ስምንተኛው ቢረሌ፥ ዘጠነኛው ወራውሬ፥ ዐሥረኛው ክርስጵራስስ፥ ዐሥራ አንደኛው ያክንት፥ ዐሥራ ሁለተኛው አሜቴስጢኖስ ነበረ።