Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 29:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እኔም እንደ ጉልበቴ ሁሉ ለአምላኬ ቤት ለወርቁ ዕቃ ወርቁን፥ ለብሩም ዕቃ ብሩን፥ ለናሱም ዕቃ ናሱን፥ ለብረቱም ዕቃ ብረቱን፥ ለእንጨቱም ዕቃ እንጨቱን፥ ደግሞ መረግድንና በፈርጥ የሚገባ ድንጋይን፥ የሚለጠፍ ድንጋይን፥ ልዩ ልዩ መልክ ያለውንም ድንጋይ፥ የከበረውንም ድንጋይ ከየዓይነቱ፥ ብዙም እብነ በረድ አዘጋጅቻለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እኔም ያለኝን ሀብት ለአምላኬ ቤተ መቅደስ ለወርቁ ሥራ ወርቁን፣ ለብሩ ሥራ ብሩን፣ ለናሱ ሥራ ናሱን፣ ለብረቱ ሥራ ብረቱን፣ ለዕንጨቱ ሥራ ዕንጨቱን እንዲሁም ለፈርጥ የሚሆነውን መረግድ፣ ኬልቄዶን፣ ልዩ ልዩ ኅብር ያላቸውን የከበሩ ድንጋዮች፣ ማንኛውንም ዐይነት የሚያምር ድንጋይና ዕብነበረድ፣ ይህን ሁሉ በብዛት አዘጋጅቻለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የምችለውን ያኽል፥ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ የሚሆኑትን ዕቃዎች ወርቅ ለወርቅ ሥራ፥ ብር ለብር ሥራ፥ ነሐስ ለነሐስ ሥራ፥ ብረት ለብረት ሥራ፥ እንጨት ለእንጨት ሥራ መርግድና የተለያዩ ቀለማት ያላቸው በፈርጥ የሚገቡ ድንጋዮች፥ የከበረ ድንጋይና በየዐይነቱ ብዙ ዕብነ በረድ አዘጋጅቼአለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እኔም እንደ ጉል​በቴ ሁሉ ለአ​ም​ላኬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወር​ቅን፥ ብርን፥ ናስን፥ ብረ​ትን፥ እን​ጨ​ትን፥ ደግ​ሞም መረ​ግ​ድ​ንና በፈ​ርጥ የሚ​ገባ ድን​ጋ​ይን፥ የሚ​ለ​ጠፍ ድን​ጋ​ይን፥ ልዩ ልዩ መልክ ያለ​ው​ንም ድን​ጋይ፥ የከ​በ​ረ​ው​ንም ድን​ጋይ ከየ​ዓ​ይ​ነቱ፥ ብዙም እብነ በረድ አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እኔም እንደ ጕልበቴ ሁሉ ለአምላኬ ቤት ለወርቁ ዕቃ ወርቁን፥ ለብሩም ዕቃ ብሩን፥ ለናሱም ዕቃ ናሱን፥ ለብረቱም ዕቃ ብረቱን፥ ለእንጨቱም ዕቃ እንጨቱን፥ ደግሞ መረግድንና በፈርጥ የሚገባ ድንጋይን፥ የሚለጠፍ ድንጋይን፥ ልዩ ልዩ መልክ ያለውንም ድንጋይ፥ የከበረውንም ድንጋይ ከየዐይነቱ፥ ብዙም እብነ በረድ አዘጋጅቻለሁ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 29:2
22 Referencias Cruzadas  

የዚያም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው፥ ሉልና የከበረም ድንጋይ በዚያ ይገኛል።


ትእዛዝህንም ምስክርህንም ሥርዓትህንም እንዲጠብቅ፥ ይህንንም ነገር ሁሉ እንዲያደርግ ያዘጋጀሁለትንም ቤት እንዲሠራ ለልጄ ለሰሎሞን ፍጹም ልብ ስጠው።”


ከዚህም በላይ ደግሞ የአምላኬን ቤት ስለወደድሁ፥ ለመቅደሱ ካዘጋጀሁት ሁሉ ሌላ የግል ገንዘቤ የሚሆን ወርቅና ብር አለኝና ለአምላኬ ቤት ሰጥቼዋለሁ።


ቤቱንም በዕንቁ አስጌጠው፤ ወርቁም የፈርዋይም ወርቅ ነበረ።


“በእውነቱ ብር የሚወጣበት፥ ወርቅም የሚነጠርበት ስፍራ አለ።


በኦፊር ወርቅ፥ በከበረም መረግድና በሰንፔር አትገመትም።


አራት ረድፍ የሆነ የዕንቁ ፈርጥ አድርግበት፤ በመጀመሪያው ረድፍ ሰርድዮን፥ ቶጳዝዮንና የሚያብረቀርቅ ዕንቁ፤


በአራተኛው ረድፍ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያስጲድ፤ በወርቅ ፈርጥ ይቀመጣሉ።


ሁለት የመረግድ ድንጋይ ወስደህ የእስራኤልን ልጆች ስም ቅረጽባቸው፤


በአራተኛውም ረድፍ ቢረሌ፥ መረግድና ኢያስጲድ በወርቅ ፈርጥ ተደረጉ።


በወርቅ ፈርጥ የተያዙ የመረግድ ድንጋዮች ሠርተው እንደ ማኅተም ቅርጽ የእስራኤልን ልጆች ስም ቀረጹባቸው።


አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምታገኘውን ሁሉ እንደ ኃይልህ አድርግ።


ዝናው በመላዋ ሶርያ ሁሉ ተሰማ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይ ተይዘው የታመሙትን ሁሉ፥ አጋንንት ያደሩባቸውን፥ በጨረቃ የሚነሣባቸውንና ሽባዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።


እንደ ዐቅማቸው መጠን፥ ዐቅማቸውም የሚያልፍ እንኳን፥ ወደው እንደ ሰጡ እመሰክርላቸዋለሁ።


ሥራችሁንም ሁሉ ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉት እንዲሁ በትጋት ፈጽሙት፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos