ለአዴርም ልጅ መልአክተኞች፦ “ለጌታዬ ለንጉሥ፥ ለእኔ ለባርያህ በመጀመሪያ የላክህብኝ ሁሉ አደርጋለሁ፥ ይህ ግን አደርገው ዘንድ አይቻለኝም በሉት” አላቸው፤ መልእክተኞችም ተመልሰው ይህን አወሩለት።
ዘፀአት 32:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንም አየውና መሠዊያን በፊቱ ሠራ፤ አሮንም፦ “ነገ የጌታ በዓል ነው” ሲል አወጀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮን ይህን ባየ ጊዜ በወርቅ ጥጃው ፊት ለፊት መሠዊያ ሠርቶ፣ “ነገ ለእግዚአብሔር በዓል ይሆናል” ብሎ ዐወጀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮንም ይህን ባየ ጊዜ በወርቁ ጥጃ ፊት መሠዊያ ሠርቶ “ነገ ለእግዚአብሔር ክብር በዓል ይደረጋል” ሲል አስታወቀ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንም በአየው ጊዜ መሠዊያውን በፊቱ ሠራ፤ አሮንም፥ “ነገ የእግዚአብሔር በዓል ነው” ሲል አወጀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንም ባየው ጊዜ መሠዊያን በፊቱ ሠራ፤ አሮንም፦ ነገ የእግዚአብሔር በዓል ነው ሲል አወጀ። |
ለአዴርም ልጅ መልአክተኞች፦ “ለጌታዬ ለንጉሥ፥ ለእኔ ለባርያህ በመጀመሪያ የላክህብኝ ሁሉ አደርጋለሁ፥ ይህ ግን አደርገው ዘንድ አይቻለኝም በሉት” አላቸው፤ መልእክተኞችም ተመልሰው ይህን አወሩለት።
እንደ ተጻፉትም ያህል በብዙ ቍጥር ፋሲካን አላከበሩም ነበርና የእስራኤልን አምላክ የጌታን ፋሲካ በኢየሩሳሌም ለማክበር እንዲመጡ ከቤር-ሳቤህ ጀምሮ እስከ ዳን ድረስ ለእስራኤል ሁሉ አዋጅ እንዲነገር ወሰኑ።
ሙሴም፦ “ወጣቶቻችን፥ ሽማግሌዎቻችን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን፥ በጎቻችንና ከብቶቻችን ከእኛ ጋር ይሄዳሉ የጌታን በዓል እናደርጋለንና” አለ።
ከእጃቸው ተቀብሎ በቅርጽ መሥሪያ ቀረጸው፥ ቀልጦ የተሠራ ጥጃ አደረገው፤ እርሱም፦ “እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብጽ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው” አላቸው።
እስራኤል ፈጣሪውን ረስቶአል፥ ቤተ መንግሥቶችን ሠርቶአል፤ ይሁዳም የተመሸጉትን ከተሞች አብዝቶአል፤ እኔ ግን በእርሱ ከተሞች ላይ እሳት እልካለሁ፥ የንጉሥ ቅጥሮቹንም ትበላለች።
በዚያም ቀን ታውጃላችሁ፤ የተቀደሰ ጉባኤም ታደርጋላችሁ። የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት። በምትቀመጡበት አገር ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ የዘለዓለም ሥርዓት ነው።
“የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የእህሉንም ቁርባን፥ መሥዋዕቱንም፥ የመጠጡንም ቁርባን፥ ለጌታም በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን፥ እያንዳንዳቸውን ተገቢ በሆነው ቀናቸው እንድታቀርቡባቸው የተቀደሱ ጉባኤዎች እንዲሆኑ የምታውጁአቸው የጌታ በዓላት እነዚህ ናቸው።