Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 32:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከእጃቸው ተቀብሎ በቅርጽ መሥሪያ ቀረጸው፥ ቀልጦ የተሠራ ጥጃ አደረገው፤ እርሱም፦ “እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብጽ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እርሱም የሰጡትን ወስዶ በመሣሪያ በመቅረጽ በጥጃ ምስል ጣዖት አድርጎ ሠራው፤ ከዚያም እነርሱ፣ “እስራኤል ሆይ፤ ከግብጽ ያወጡህ አማልክት እነዚህ ናቸው” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እርሱም የወርቅ ጒትቻውን ሁሉ ወስዶ በእሳት አቀለጠው፤ የቀለጠውንም ወርቅ በቅርጽ መሥሪያ ውስጥ አግብቶ የወርቅ ጥጃ አድርጎ ሠራው። እነርሱም “እስራኤል ሆይ! ከግብጽ ምድር መርቶ ያወጣን አምላካችን ይህ ነው!” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከእ​ጃ​ቸ​ውም ተቀ​ብሎ በመ​ቅ​ረጫ ቀረ​ጸው፤ ቀልጦ የተ​ሠራ ጥጃም አደ​ረ​ገው፤ እር​ሱም፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እነ​ዚህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጡህ አማ​ል​ክ​ትህ ናቸው” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከእጃቸውም ተቀብሎ በመቅረጫ ቀረጸው፥ ቀልጦ የተሠራ ጥጃም አደረገው፤ እርሱም፦ እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው አላቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 32:4
36 Referencias Cruzadas  

በዚህም ጉዳይ ከመከረበት በኋላ የሁለት ጥጆችን ምስል ከወርቅ አሠርቶ ለሕዝቡ “ከዚህ በፊት ታደርጉት በነበረው ዓይነት ለመስገድ እስከ ኢየሩሳሌም መሄድ ይበቃችኋል፤ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ከግብጽ ምድር ያወጡህ አማልክትህ እነሆ እነዚህ ናቸው!” አለ።


ኢዮርብዓም በይሁዳ በሚደረገው በዓል ዓይነት ስምንተኛው ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን የባዕድ አምልኮ በዓል እንዲደረግ ወሰነ፤ ከወርቅ ላሠራቸውም ምስሎች በቤትኤል በሚገኘው መሠዊያ ላይ ለጥጃው ምስል መሥዋዕት አቀረበ፤ በዚያም በቤትኤል ለማምለኪያ ባሠራቸው ስፍራዎች የሚያገለግሉ ካህናትን መደበ።


ከዚህም በኋላ ኢዩ “በዓል ተብሎ ለሚጠራው ጣዖት ክብረ በዓል ይደረግ!” ሲል ትእዛዝ ሰጠ፤ ይህም በዐዋጅ ተነገረ።


ነገር ግን ኢዩ እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራውን የንጉሥ ኢዮርብዓምን የኃጢአት መንገድ ከመከተል አልተገታም፤ ኢዩ ራሱ ቀደም ሲል የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በቤትኤልና በዳን ላቆማቸው የወርቅ ጥጃ ምስሎች መስገዱ አልቀረም።


እርሱ ግን ለኮረብታው መስገጃዎች ለአጋንንቱም ለሠራቸውም እምቦሶች ካህናትን ሾመ።


“እንግዲህ አሁን እናንተ እጅግ ታላቅ ሕዝብ ናችሁና፥ ኢዮርብዓምም አማልክት አድርጎ የሠራላችሁ የወርቅ እምቦሶች ከእናንተ ጋር ናቸውና በዳዊት ልጆች እጅ የሚሆነውን የጌታን መንግሥት ልትቋቋሙ ታስባላችሁ።


ከቀለጠ ብረት የተቀረጸ ጥጃ ሠርተው “ከግብጽ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው” አሉ፥ ብዙ ተሳደቡ፥


“ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ ጌታ አምላክህ እኔ ነኝ።


ከእኔ ጋር የብር አማልክትን አትሥሩ፥ የወርቅ አማልክትንም ለእናንተ አትሥሩ።


በላይ በሰማያት ካለው፥ በታች በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም አምሳል፥ የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ።


በቅርጽ ሠራተኛ ሥራ እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገህ የእስራኤልን ልጆች ስም በሁለት ድንጋዮች ቅረጽ በወርቅ ፈርጥ ሥራቸው።


ሁለት የመረግድ ድንጋይ ወስደህ የእስራኤልን ልጆች ስም ቅረጽባቸው፤


ሕዝቡ ሙሴ ከተራራው ሳይወርድ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ፥ ወደ አሮን ተሰብስበው፦ “ይህ ከግብጽ ምድር ያወጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ደረሰበት አናውቅም፤ ስለዚህ ተነሥና በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን” አሉት።


እኔም፦ ‘ከእናንተ ወርቅ ያለው ሰው ሁሉ ሰብሮ ያምጣልኝ’ አልኋቸው፤ እነርሱም ሰጡኝ፥ በእሳት ላይ ጣልሁት፥ ይህም ጥጃ ወጣ።”


ሕዝቡ ሁሉ በጆሮቻቸው ያሉትን የወርቅ ቀለበቶች ሰብረው ወደ አሮን አመጡለት።


አሮን የሠራውን ጥጃ ስለ ሠሩ ጌታ ሕዝቡን ቀሠፈ።


አሮንም አየውና መሠዊያን በፊቱ ሠራ፤ አሮንም፦ “ነገ የጌታ በዓል ነው” ሲል አወጀ።


ጌታ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከግብጽ ምድር ያወጣኸው ሕዝብህ በድለዋልና ሂድ ውረድ፤


ካዘዝኋቸው መንገድ ፈጥነው ፈቀቅ አሉ፤ ለራሳቸውም ቀልጦ የተሠራ ጥጃ ሠሩ፥ ሰገዱለት፥ ሠዉለትም፦ ‘እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብጽ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው’ አሉ።”


በብርም የተለበጡትን የተቀረጹትን ምስሎችህን፥ በወርቅም የተለበጡትን ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎችህን ታረክሳለህ፤ እንደ ርኩስም ነገር ትጥላቸዋለህ፦ “ከእኔ ራቁ!” ትላቸዋለህ።


ወርቁን ከኮሮጆ የሚያፈስሱ፥ ብሩንም በሚዛን የሚመዝኑ እነርሱ አንጥረኛውን ይቀጥራሉ፤ እርሱም አምላክ አድርጎ ይሠራዋል፤ ለዚያም ይጐነበሱለታል ይሰግዱለትማል።


ከግብጽ ጀምሮ የነበረውን አመንዝራነቷን አልተወችም፤ በወጣትነትዋ ጊዜ ወንዶች ከእርሷ ጋር ተኝተው ነበርና፥ የድንግልናዋንም የጡቶቿ ጫፎች ዳብሰው ነበርና፥ ፍትወታቸውንም አፍስሰውባት ነበርና።


የሰማርያ ሰዎች የቤትአዌንን እምቦሳ ፈሩ፤ ክብሩ ከእርሱ ተለይቶታልና ሕዝቡ ያለቅሱለታል፥ የጣዖቱ ካህናትም እሪ ብለው ይጮኹለታል።


አሁንም ኃጢአትን እጅግ አብዝተው ይሠራሉ፤ በብራቸውም ለራሳቸው ቀልጦ የተሠራ ምስልን፥ እንደ ጥበባቸውም ጣዖታትን ሠርተዋል፤ ሁሉም የሞያተኞች ሥራ ናቸው። ስለ እነርሱም የሚሠዉ ሰዎች፦ “እምቦሳውን ይሳሙ” ይላሉ።


እንግዲህ የእግዚአብሔር ዘመዶች ከሆንን፥ አምላክ በሰው ብልሃትና አሳብ የተቀረጸውን ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ እንዲመስል እናስብ ዘንድ አይገባንም።


በዚያም ወራት ጥጃ አድረጉ፤ ለጣዖቱም መሥዋዕት አቀረቡ፤ በእጃቸውም ሥራ ደስ አላቸው።


“ሕዝቡም ሊበሉ ሊጠጡም ተቀመጡ፤ ሊዘፍኑም ተነሡ፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንዳደረጉት ጣዖትን የምታመልኩ አትሁኑ።


ተመለከትሁም፥ እነሆ፥ አምላካችሁን ጌታ በድላችሁ ነበር፥ ለእናንተም ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ምስል ሠርታችሁ ነበር፤ ጌታ ካዘዛችሁ መንገድ ፈጥናችሁ ፈቀቅ ብላችሁ ነበር።


እርሱም “አንድ የምጠይቃችሁ ነገር አለኝ፤ ይኸውም እያንዳንዳችሁ ከምርኮ ካገኛችሁት ውስጥ የጆሮ ጉትቻችሁን እንድትሰጡኝ ነው” አላቸው፤ የወርቅ ጉትቻ ማድረግ የእስማኤላውያን ባህል ነበርና።


ጌዴዎን በወርቁ ኤፉድ ሠራ፤ በተወለደበትም ከተማ በዖፍራ አኖረው። እስራኤልም በሙሉ ኤፉዱን በማምለክ ስላመነዘሩ፥ ኤፉዱ ለጌዴዎንና ለቤተ ሰቡ ወጥመድ ሆነ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos