የእግዚአብሔር መልአክም አላት፦ እነሆ አንቺ ፀንሰሻል፥ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም እስማኤል ብለሽ ትጠሪዋለሽ፥ እግዚአብሔር መቸገርሽን ሰምቶአልና።
ዘፀአት 2:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከብዙ ቀኖች በኋላ የግብጽ ንጉሥ ሞተ፤ የእስራኤልም ሕዝቦች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፥ ጮኹም፥ ስለባርነታቸውም የልመና ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከብዙ ዓመት በኋላ የግብጽ ንጉሥ ሞተ፤ እስራኤላውያንም በባርነት ከደረሰባቸው ግፍ የተነሣ ይጮኹ ነበር፤ ከባርነት ቀንበር ለመላቀቅ ያሰሙትም ጩኸት ወደ እግዚአብሔር ደረሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብዙ ዓመቶች በኋላ የግብጽ ንጉሥ ሞተ፤ እስራኤላውያን ግን አሁንም በባርነት ቀንበር ሥር በመጨነቅ ርዳታ ለማግኘት በመጮኽ ላይ ነበሩ፤ ጩኸታቸውም ወደ እግዚአብሔር ደረሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ከብዙ ቀን በኋላ እንዲህ ሆነ፤ የግብፅ ንጉሥ ሞተ፤ የእስራኤልም ልጆች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፤ ጮኹም፤ ስለ ባርነታቸውም ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም ከብዙ ቀን በኋላ እንዲህ ሆነ፤ የግብፅ ንጉሥ ሞተ፤ የእስራኤልም ልጆች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፤ ጮኹም፤ ስለባርነታቸውም ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ። |
የእግዚአብሔር መልአክም አላት፦ እነሆ አንቺ ፀንሰሻል፥ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም እስማኤል ብለሽ ትጠሪዋለሽ፥ እግዚአብሔር መቸገርሽን ሰምቶአልና።
ይህም ለሠራዊት ጌታ በግብጽ ምድር ምልክትና ምስክር ይሆናል፤ ከሚያስጨንቁአቸው ምክንያት ወደ ጌታ በመጮኻቸው፥ እርሱ መድኃኒትንና ኃያልን ሰዶ ያድናቸዋል።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የወይን ቦታ የእስራኤል ቤት ነው፤ የይሁዳ ሰዎችም የደስታው አትክልት ናቸው። ፍትሕን ፈለገ፤ ነገር ግን ደም ማፍሰስን አየ፤ ጽድቅን ፈለገ፤ ነገር ግን የጭንቅን ጩኸት ሰማ።
ያዕቆብ ወደ ግብጽ ከገባ በኋላ፥ አባቶቻችሁ ጌታ እንዲረዳቸው ወደ እርሱ ጮኹ፤ ጌታም የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር አውጥተው በዚህ ስፍራ እንዲኖሩ ያደረጉትን ሙሴንና አሮንን ላከላቸው።
“ነገ በዚህ ጊዜ ከብንያም ምድር አንድ ሰው ወደ አንተ እልካለሁ፤ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ እንዲሆን ቀባው፤ እርሱም ሕዝቤን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ይታደጋል። እነሆ፤ ሕዝቤን ከላይ ተመልክቻለሁ፤ የስቃይ ጩኸቱ ከእኔ ዘንድ ደርሷልና።”