Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 35:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከግፍ ብዛት የተነሣ ሰዎች ይጮኻሉ፥ ከኃያላንም ክንድ የተነሣ ለእርዳታ ይጣራሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “ሰው ከጭቈና ብዛት የተነሣ ይጮኻል፤ ከኀያሉም ክንድ ሥር ለመውጣት ለርዳታ ይጣራል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ሰዎች ጭቈና ሲበዛባቸው ይጮኻሉ፤ ከሚበረታባቸውም እጅ የሚታደጋቸውን ለማግኘት፥ አቤቱታ ያሰማሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ከግ​ፈ​ኞች ብዛት የተ​ነሣ ሰዎች ይጮ​ኻሉ፤ ከብ​ዙ​ዎች ክንድ የተ​ነ​ሣም ለር​ዳታ ይጠ​ራሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ከግፍ ብዛት የተነሣ ሰዎች ይጮኻሉ፥ ከኃያላንም ክንድ የተነሣ ለእርዳታ ይጠራሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 35:9
20 Referencias Cruzadas  

ከብዙ ቀኖች በኋላ የግብጽ ንጉሥ ሞተ፤ የእስራኤልም ሕዝቦች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፥ ጮኹም፥ ስለባርነታቸውም የልመና ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ።


አንተ አምላኬ ኃይሌም፥ ለምን ትተወኛለህ? ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን አዝኜ እመላለሳለሁ?


ምላሳችንን እናበረታለን፥ ከንፈራችን የእኛ ነው፥ ጌታችን ማን ነው? የሚሉትን።


የክፉዉንና የግፈኛውን ክንድ ሰባብር፥ ምንም እስከማይገኝ ድረስ ክፋቱን ፈልገህ አግኝ።


እንደ እግዚአብሔር ክንድ ያለ ክንድ አለህን? ወይስ እንደ እርሱ ባለ ድምፅ ታንጐደጉዳለህን?


በከተማው ለመሞት የሚያጣጥሩ ያቃስታሉ፥ ቁስለኞችም ለእርዳታ ይጮኻሉ፥ እግዚአብሔር ግን ልመናቸውን አይመለከትም።”


ካህናትን እንደ ምርኮኛ ይወስዳቸዋል፥ ኃያላንንም ይገለብጣቸዋል።


አሁን ደግሞ የእስራኤል ልጆች ጩኸት ወደ እኔ መጣ፤ ግብፃውያን የሚያደርጉባቸውን ግፍ ደግሞ አየሁ።


ጌታም አለ፦ “በግብጽ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፥ በአስገባሪዎቻቸውም ምክንያት የሚጮሁትን ጩኸት ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ።


ቁጣዬም ይነዳል፥ በሰይፍም እገድላችኋለሁ፥ ሚስቶቻችሁ መበለት፥ ልጆቻችሁም ድሀ አደጎች ይሆናሉ።


የሠራበትን ሒሣብ በዕለቱ፥ ፀሓይ ሳትጠልቅ ክፈለው፤ ድኻ በመሆኑ በጉጉት ይጠባበቀዋል። ያለበለዚያ ወደ ጌታ ይጮኽና ኃጢአት ይሆንብሃል።


ድሀውን ረግጦአል፥ ትቶታልም፥ ያልሠራውንም ቤት በዝብዞአል።”


ክፋትህ እንደ አንተ ያለውን ሰው ይጐዳዋል፥ ለሰውም ልጅ ጽድቅህ ይጠቅመዋል።


እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፥ እነሆም፥ የተገፉት ሰዎች እንባ፥ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፥ በሚገፉአቸውም እጅ ኃይል ነበረ፥ እነርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም።


በመኝታቸው ላይ ሆነው ያለቅሱ ነበር እንጂ በልባቸው ወደ እኔ አልጮኹም፤ ስለ እህልና ስለ ወይን ጠጅ ይሰበሰቡ ነበር፤ በእኔም ላይ ዓመፁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios