La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 17:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱም የዚያን ስፍራ ስም ማሳህና መሪባ ብሎ ጠራው፥ ይህም ስለ እስራኤል ልጆች ጥልና “ጌታ በመካከላችን ነው ወይስ አይደለም?” በማለት ጌታን ስለተፈታተኑት ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስፍራውንም ማሳህና መሪባ ብሎ ጠራው፤ እስራኤላውያን ጠብ ፈጥረው፣ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው ወይስ አይደለም” በማለት እግዚአብሔርን ተፈታትነዋልና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እስራኤላውያን “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ወይስ አይደለም?” በማለት በማጒረምረማቸውና እግዚአብሔርን በመፈታተናቸው ያ ስፍራ ማሳህና እና መሪባ ተብሎ ተጠራ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ስለ እስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ክር​ክር፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችን ነውን? ወይስ አይ​ደ​ለም?” ሲሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ ተፈ​ታ​ተ​ኑት የዚ​ያን ስፍራ ስም “መን​ሱት” ደግ​ሞም “ጋእዝ” ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስለ እስራኤልም ልጆች ክርክር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን ነውን ወይስ አይደለም? ሲሉ እግዚአብሔርን ስለተፈታተኑት የዚያን ስፍራ ስም ማሳህ፥ ደግሞም መሪባ ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo



ዘፀአት 17:7
21 Referencias Cruzadas  

በክርክር ውኃ ዘንድም አስቈጡት፥ መንፈሱን አስመርረዋታልና፥ በእነርሱም የተነሣ ሙሴ ተበሳጨ፥ በከንፈሮቹም ያለማስተዋል ተናገረ።


የተመኙትን መብል እየጠየቁ፥ እግዚአብሔርን በልባቸው ፈተኑት።


ጫንቃውን ከሸክም፥ እጆቹንም በቅርጫት ከመገዛት አራቅሁ።


በመከራህ ጊዜ ጠራኸኝ አዳንሁህም፥ ከተሰወረ የሞገድ ስፍራ መለስሁልህ፥ በክርክር ውኃ ዘንድም ፈተንሁህ።


በምድረ በዳ፥ በመሪባና በማሳ እንዳደረጋችሁት፥ ልባችሁን አታጽኑ።


ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፦ “የምንጠጣውን ውኃ ስጠን” አሉት። ሙሴም፦ “ለምን ትጣሉኛላችሁ? ጌታንስ ለምን ትፈታተናላችሁ?” አላቸው።


እንዲህም አለ፦ “ጌታ ሆይ በፊትህ ሞገስን አግኝቼ ከሆነ፥ ይህ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ነውና እባክህን ጌታ በመካከላችን ይሂድ፤ በደላችንንና ኃጢአታችንን ይቅር በለን፥ ርስትህ አድርገህ ተቀበለን።”


የጽዮን ሕዝብ ሆይ፤ እልል በሉ፤ በደስታም ዘምሩ፤ በመካከላችሁ ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ነውና።”


አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቷ በክፍያ ያስተምራሉ፥ ነቢዮችዋ በብር ያሟርታሉ፤ “ጌታ በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር በእኛ ላይ አይመጣብንም” እያሉ በጌታ ይደገፋሉ።


በግብጽ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግሁትን ክብሬንና ተአምራቴን ያዩ እነዚህ ሰዎች ሁሉ ዐሥር ጊዜ እኔን ስለ ተፈታተኑኝ፥ ድምፄንም ስላልሰሙ፥


የእስራኤል ልጆች ከጌታ ጋር የተጣሉበት፥ እርሱም በመካከላቸው ቅዱስ መሆኑን የገለጠበት ይህ የመሪባ ውኃ ነው።


“አሮን ወደ ወገኑ ይከማች፤ በመሪባ ውኃ ዘንድ በትእዛዜ ላይ ስላመፃችሁ ለእስራኤል ልጆች ወደ ሰጠኋት ምድር አይገባም።


እናንተ በጺን ምድረ በዳ ማኅበሩ በተገዳደረኝ ጊዜ በቃሌ ላይ ዐምፃችኋልና፥ በእነርሱም ፊት በውኃው ዘንድ አልቀደሳችሁኝምና።” ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ያለው የመሪባ ውኃ ነው።


ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በእኛም ዘንድ አደረ፤ ጸጋንና እውነትን የተመላውን፥ የአባቱ አንድያ ልጅ በአባቱ ዘንድ ያለውን ክብሩንም አየን።


በዚያች ቀን እቀጣቸዋለሁ፤ እተዋቸዋለሁም፤ ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ እነርሱም ይጠፋሉ። ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር ይደርስባቸዋል፤ በዚያችም ቀን፥ ‘ይህ ጥፋት የደረሰብን፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባለመሆኑ አይደለምን?’ ይላሉ።


ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፦ “ማሳህ በተባለው ቦታ ለፈተንኸው፥ በመሪባ ውኃም ለተከራከርኸው፥ ቱሚምህን ለሌዊ ስጠው፥ ኡሪምህም ለዚህ ቅዱስ ሰው ነው፤


“ ‘በማሳህ’ እንደ ፈተናችሁት ጌታ አምላካችሁን አትፈታተኑት።


“እንደገና በታቤራ፥ በማሳህም፥ በቂብሮት ሐታዋም ጌታን አስቆጣችሁት።


የካህኑም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ለሮቤል ልጆችና ለጋድ ልጆች ለምናሴም ልጆች እንዲህ አላቸው፦ “ይህን መተላለፍ በጌታ ላይ አላደረጋችሁምና ጌታ በመካከላችን እንዳለ ዛሬ አውቀናል፤ አሁን የእስራኤልን ልጆች ከጌታ እጅ አድናችኋል።”