ኤፌሶን 5:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁ፤ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፤ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁ፤ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ። እንደ ብርሃን ልጆች ኑሩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀድሞ እናንተ በጨለማ ውስጥ ትኖሩ ነበር፤ አሁን ግን የጌታ ስለ ሆናችሁ ብርሃን ናችሁ ስለዚህ በብርሃን እንደሚኖሩ ሰዎች ተመላለሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ ዛሬ ግን በጌታችን ብርሃን ሆናችኋል። እንግዲህስ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፤ |
ዕውሮችንም በማያውቁት መንገድ አመጣቸዋለሁ፤ በማያውቁትም ጎዳና እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፤ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህን አደርግላቸዋለሁ፥ አልተዋቸውም።
እርሱም፦ “የያዕቆብን ነገዶች እንድታስነሣ ከእስራኤልም የተረፉትን እንድትመልስ አገልጋዬ እንድትሆን እጅግ ቀላል ነገር ነውና ማዳኔ እስከ ምድር ዳር እንዲደርስ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ ይላል።
የተሰሩትንም፦ ‘ውጡ’ በጨለማም የተቀመጡትን፦ ‘ተገለጡ’ እንድትል ቃል ኪዳን አድርጌ ለሕዝቡ ሰጥቼሃለሁ። በመንገድም ላይ ይሰማራሉ፥ ማሰማርያቸውም በገላጣ ኮረብታ ሁሉ ላይ ይሆናል።
ከእናንተ ጌታን የሚፈራ፥ የአገልጋዩንም ቃል የሚሰማ፥ በጨለማም የሚሄድ፥ ብርሃንም የሌለው፥ ነገር ግን በጌታ ስም የሚታመን፥ በአምላኩም የሚደገፍ ማን ነው?
ሕዝብን አበዛህ፤ ደስታቸውንም ጨመርህ፤ ሰዎች ምርትን ሲሰበስቡ፤ ምርኮንም ሲከፋፈሉ ደስ እንደሚላቸው ሁሉ፤ እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል።
ሳትጨልም እግራችሁም በጨለሙት ተራሮች ላይ ሳትሰናከል፥ በተስፋ የምትጠባበቁትን ብርሃን ለሞት ጥላና ለድቅድቅ ጨልማ ሳይለውጠው፥ ለአምላካችሁ ለጌታ ክብርን ስጡ።
ኢየሱስም “ገና ጥቂት ጊዜ ብርሃን ከእናንተ ጋር ነው። ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማም የሚመላለስ ወዴት እንዲሄድ አያውቅም።
ምክንያቱም እግዚአብሔርን እያወቁት እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን አላከበሩትም ወይም አላመሰገኑትም፤ ነገር ግን ምክንያታቸው ዋጋ ቢስ ሆነ፤ የማያስተውለው ልባቸውም ጨለመ።
እኛም ሁላችን፥ በመጋረጃ በማይሸፈን ፊት፥ የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን፥ የእርሱን መልክ እንድንመስል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን፥ ይህም መንፈስ ከሚሆን ጌታ የመጣ ነው።
በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት እንዲሰጥ ብርሃን በልባችን ውስጥ ያበራ፥ “በጨለማ ብርሃን ይብራ፤” ያለው እግዚአብሔር ነው።
በዚህም የዚህን ዓለም አኗኗር በመከተል፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው፥ በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ እየታዘዛችሁ ትኖሩ ነበር።
ክርስቶስም እንዳፈቀራችሁ፥ ስለ እናንተም ለእግዚአብሔር መልካም መዓዛ ያለው መባንና መሥዋዕት አድርጎ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ፥ በፍቅር ተመላለሱ።
ተጋድሏችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለም፤ ነገር ግን ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር፥ ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር፥ በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው።
እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባርያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት ጊዜያችንን የምናሳልፍ፥ የምንጠላ፥ እርስ በርሳችንም የምንጠላላ ነበርን።
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ እርስ በእርሳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።