ኤልዛቤል የጌታን ነቢያት ታስገድል በነበረችበትም ጊዜ አብድዩ አንድ መቶ የሚሆኑትን የእግዚአብሔርን ነቢያት ከሁለት ከፍሎ ኀምሳ፥ ኀምሳውን በዋሻዎች ከሸሸጋቸው በኋላ እህልና ውሃ በማቅረብ ይመግባቸው ነበር።
ዘዳግም 23:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክንያቱም ከግብጽ ከወጣችሁ በኋላ በጉዞ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ እህል ውሃ ይዘው አልተቀበሏችሁም፤ በመስጴጦምያ በምትገኘው በፐቶር ይኖር የነበረውን የቢዖርን ልጅ በለዓምም አንተን እንዲረግም በገንዘብ ገዝተውት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም ከግብጽ ከወጣችሁ በኋላ በጕዞ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ እህል ውሃ ይዘው አልተቀበሏችሁም፤ በመስጴጦምያ በምትገኘው በፐቶር ይኖር የነበረውን የቢዖር ልጅ በለዓምን አንተን እንዲረግም በገንዘብ ገዙት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ከግብጽ ምድር ወጥታችሁ በጒዞ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ እነርሱ እህልና ውሃ አንሰጥም ብለው ከልክለዋችሁ እንደ ነበር አይዘነጋም፤ ከዚሁም ጋር በመስጴጦምያ ፐቶር ተብላ በምትጠራው ከተማ ይኖር የነበረ የቢዖር ልጅ በለዓም እንዲረግማችሁ ቀጥረውት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ እንጀራና ውኃ ይዘው በመንገድ ላይ አልተቀበሉአችሁምና፥ ከመስጴጦምያ የቢዖርን ልጅ በለዓምን ዋጋ ሰጥተው ይረግማችሁ ዘንድ ተዋውለውባችኋልና። |
ኤልዛቤል የጌታን ነቢያት ታስገድል በነበረችበትም ጊዜ አብድዩ አንድ መቶ የሚሆኑትን የእግዚአብሔርን ነቢያት ከሁለት ከፍሎ ኀምሳ፥ ኀምሳውን በዋሻዎች ከሸሸጋቸው በኋላ እህልና ውሃ በማቅረብ ይመግባቸው ነበር።
እነዚህ ነገሮች ከተፈጸሙ በኋላ አለቆቹ ወደ እኔ ቀርበው፦ “የእስራኤል ሕዝብ፥ ካህናቱና ሌዋውያኑም እንደ ከነዓናውያን፥ ሒቲያውያን፥ ፌርዛውያን፥ ኢያቡሳውያን፥ አሞናውያን፥ ሞዓባውያን፥ ግብጻውያንና አሞራውያን ርኩሰት ያደርጋሉ እንጂ ከምድር ሕዝቦች እራሳቸውን አልለዩም፤
ይህም ደግሞ የእስራኤልን ልጆች በምግብና በውኃ ስላልተቀበሉአቸውና እንዲረግማቸውም በለዓምን ስለ ገዙት ነው፤ ነገር ግን አምላካችን እርግማኑን ወደ በረከት ለወጠው።
ስለ አሞን ልጆች፤ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ለእስራኤል ልጆች የሉትምን? ወይስ ወራሽ የለውምን? ታዲያ ሚልኮምስ ጋድን ለምን ወረሰ? ሕዝቡስ በከተሞቹ ላይ ለምን ተቀመጠ?
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእስራኤል ልጆች መካከል ያለ የባዕድ ልጅ ሁሉ፥ ልቡ ያልተገረዘ ሥጋው ያልተገረዘ የባዕድ ልጅ ሁሉ ወደ መቅደሴ አይግባ።
በለዓምም ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “ባላቅ ከአራም አመጣኝ፥ የሞዓብ ንጉሥ ከምሥራቅ ተራሮች፤ ‘ና፥ ያዕቆብን ርገምልኝ፤ ና፥ እስራኤልን አውግዝልኝ አለኝ።’
ንጉሡም እንዲህ ሲል ይመልስላቸዋል ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ለሚያንሱት ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ያደረጋችሁት ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው።’
ታዲያ እንጀራዬንና ውሃዬን እንዲሁም በጎቼን ለሚሸልቱልኝ ሰዎች ያረድሁትን ፍሪዳ ከየት እንደመጡ ለማይታወቁ ሰዎች የምሰጠውስ ለምንድን ነው?”