ዘዳግም 2:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብቻ ጌታ አምላካችን ወደ ከለከለን፥ ወደ አሞን ልጆች ምድር በያቦቅም ወንዝ አጠገብ ወዳለው ስፍራ ሁሉ በተራራማውም አገር ወዳሉት ከተሞች አልቀረብንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ አምላካችን እግዚአብሔር በሰጠው ትእዛዝ መሠረት፣ ወደ ማንኛውም የአሞናውያን ምድር ወይም በያቦቅ ወንዝ መውረጃ ወዳለው ምድር ወይም ደግሞ በኰረብቶች ወዳሉት ከተሞች ዙሪያ ዐልፋችሁ አልሄዳችሁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ወደ ዐሞናውያን ግዛት አጠገብ ወይም ወደ ያቦቅ ወንዝ ዳርቻ ወይም ወደ ኮረብታማይቱ አገር ከተሞች ወይም እግዚአብሔር እንዳንደርስባቸው ወዳዘዘን እነዚህን ከመሳሰሉት አገሮች ወደ አንዲቱ እንኳ አልቀረብንም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳሩ ግን አምላካችን እግዚአብሔር እንዳዘዘን ወደ አሞን ልጆች ምድር፥ በያቦቅም ወንዝ አጠገብ ወደ አለው ስፍራ ሁሉ፥ በተራራማውም ሀገር ወደ አሉ ከተሞች አልደረስንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳሩ ግን አምላካችን እግዚአብሔር ወደ ከለከለን ሁሉ፥ ወደ አሞን ልጆች ምድር በያቦቅም ወንዝ አጠገብ ወዳለው ስፍራ ሁሉ በተራራማውም አገር ወዳሉት ከተሞች አልደረስንም። |
በአሞን ልጆች አቅራቢያ ስትደርስ፥ ለሎጥም ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከአሞን ልጆች ምድር ርስት አልሰጥህምና፥ አትጣላቸው አትውጋቸውም።’”
ጌታም አለኝ፦ ‘እኔ ዔርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ፥ ከእነርሱ ምድር ምንም አልሰጣችሁምና ሞዓባውያንን አትጣላ በውጊያም አትጋፈጣቸው።’”
ለሮቤልና ለጋድም ነገዶች ከገለዓድ ጀምሮ እስከ አርኖን ሸለቆ ድረስ፥ የሸለቆውን አማካይ እንደ ወሰን፥ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ እስከ ያቦቅ ወንዝ ድረስ ሰጠሁ፤
በሐሴቦን የተቀመጠው የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎን፥ ይገዛ የነበረው በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም መካከል ጀምሮ የገለዓድን እኩሌታ እስከ ያቦቅ ወንዝ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ ሲሆን፥