Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 3:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 “ከዚያ ተመልሰን በባሳን መንገድ ወጣን፥ የባሳን ንጉሥ ዖግም፥ እርሱና ሕዝቡም ሁሉ፥ በኤድራይ ሊዋጉን ወጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከዚያም ተመልሰን ወደ ባሳን የሚወስደውን መንገድ ይዘን ወጣን፤ የባሳን ንጉሥ ዐግም ከመላው ሰራዊቱ ጋራ ሆኖ በኤድራይ ጦርነት ሊገጥመን ተነሣ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 “ቀጥለንም በስተሰሜን በኩል ወደ ባሳን ግዛት ተጓዝን፤ ንጉሥ ዖግም ሕዝቡን ሁሉ አሰልፎ በኤድረዒ ከተማ ከእኛ ጋር ለመዋጋት ወጣ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “ተመ​ል​ሰ​ንም በባ​ሳን መን​ገድ ወጣን፤ የባ​ሳን ንጉሥ ዐግም፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ በኤ​ድ​ራ​ይን ሊዋ​ጉን ወጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ተመልሰን በባሳን መንገድ ወጣን፥ የባሳን ንጉሥ ዐግም ሕዝቡም ሁሉ በኤድራይ ሊዋጉን ወጡ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 3:1
15 Referencias Cruzadas  

ወደዚህም ስፍራ በደረሳችሁ ጊዜ፥ የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎንና የባሳን ንጉሥ ዐግ ሊወጉን መጡ፤ ነገር ግን ድል አደረግናቸው።


በሐሴቦን ተቀምጦ የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፥ በአስታሮትና በኤድራይ ተቀምጦ የነበረውን የባሳንን ንጉሥ ዐግን ከመታ በኋላ፥


የባሳንን ንጉሥ ዐግን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥


“መንግሥታትንና አሕዛብን ሰጠሃቸው፤ የሐሴቦንን ንጉሥ የሴዎንን ምድር፥ የባሳንንም ንጉሥ የዐግን ምድር ወረሱ።


ጌቤር የተባለው የኡሪ ልጅ፦ በአሞራውያን ንጉሥ ሲሖንና በባሳን ንጉሥ ዖግ ትገዛ የነበረችው የገለዓድ ግዛት አስተዳዳሪ። እነዚህን ዐሥራ ሁለቱን አስተዳዳሪዎች የሚቆጣጠር በመላ አገሪቱ ሌላ አንድ የበላይ ኀላፊ ነበር።


ግዛታቸውም ከመሃናይም ጀምሮ የባሳን ንጉሥ የዐግ መንግሥት፥ ባሳን ሁሉ፥ በባሳንም ያሉት የኢያዕር መንደሮች ሁሉ ስድሳው ከተሞች፥


ከራፋይምም ወገን የቀረ፥ በአስታሮትና በኤድራይ የተቀመጠው የባሳን ንጉሥ ዐግ፥


በዮርዳኖስ ማዶም በነበሩት በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት በሐሴቦን ንጉሥ በሴዎን በአስታሮትም በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል።


ጌታ የአሞራውያንን ነገሥታት ሴዎንንና ዐግን ከነምድራቸው እንዳጠፋቸው እነዚህንም ያጠፋቸዋል።


እነርሱም የእርሱን ምድርና እንዲሁም በዮርዳኖስ ምሥራቅ የምትገኘውን ባሳንን ይገዛ የነበረውን የሌላውን አሞራዊ ንጉሥ የዖግን ምድር ወረሱ።


ጌታም፦ ‘እርሱንና ሕዝቡን ሁሉ ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአለሁና አትፍራው፥ በሐሴቦን ይኖር በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሲሖን ላይ እንዳደረግህ በእርሱም ታደርግበታለህ’ አለኝ።”


ሴዎንም፥ እሱና ሕዝቡም ሁሉ፥ ሊጋጠሙን ወደ ያሐጽ ወጡ።


የእስራኤልም ልጆች ያሸነፉአቸው፥ ከአርኖንም ሸለቆ ጀምሮ እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ በምሥራቅ ያለውን ዓረባ ሁሉ በዮርዳኖስም ማዶ በፀሐይ መውጫ ያለውን አገራቸውን የወረሱአቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios