ከእነርሱም በኋላ፥ ዐቅመ ደካማ፥ መልካቸው እጅግ የከፋና ዐጥንታቸው የወጣ ሌሎች ሰባት ላሞች ወጡ፤ እነዚያን የመሰሉ የሚያስከፋ መልክ ያላቸው ላሞች በግብጽ ምድር ከቶ አይቼ አላውቅም።
ዘዳግም 17:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በአምላክህ በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነውና፥ ከበሬ ወይም ከበግ ነውር ወይም ጉድለት ያለበትን ለአምላክህ ለጌታ አትሠዋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንከን ወይም ጕድለት ያለበትን በሬ ወይም በግ በርሱ ዘንድ አስጸያፊ ነውና ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አትሠዋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከከብት ወይም ከበግ መንጋዎች መካከል አንዳች ነውር ያለበትን እንስሳ ለእግዚአብሔር ለአምላክህ መሥዋዕት አድርገህ አታቅርብ፤ ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና ነውር ወይም ክፉ ነገር ያለበትን በሬ ወይም በግ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አትሠዋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነውና ነውር ወይም ክፉ ነገር ያለበትን በሬ ወይም በግ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አትሠዋ። |
ከእነርሱም በኋላ፥ ዐቅመ ደካማ፥ መልካቸው እጅግ የከፋና ዐጥንታቸው የወጣ ሌሎች ሰባት ላሞች ወጡ፤ እነዚያን የመሰሉ የሚያስከፋ መልክ ያላቸው ላሞች በግብጽ ምድር ከቶ አይቼ አላውቅም።
“መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከበሬ መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በጌታ ፊት እንዲሠምርለት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል።
“የታወረውን ለመሥዋዕት ስታቀርቡ፥ ይህ ክፉ አይደለምን? አንካሳውንና የታመመውን ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? ይህንን ለገዢህ አቅርብ፤ በውኑ በአንተ ደስ ይለዋልን? ወይስ ፊትህንስ ይቀበላልን?” ይላል የሠራዊት ጌታ።
ለጌታም መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ አንድ ወይፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ፤ ነውር የሌለባቸውም ይሁኑ።
አንድ እንስሳ እንከን ያለው፥ አንካሳ ወይም ዕውር፥ ወይም ደግሞ ማናቸውም ዓይነት ከባድ ጉድለት ያለበት ከሆነ ለጌታ ለእግዚአብሔር አትሠዋው፤
ስለ ተሳልኸው ስእለት ሁሉ የአመንዝራይቱን ዋጋና የውሻውን ዋጋ ወደ አምላክህ ወደ ጌታ ቤት አታቅርብ፥ ሁለቱም በጌታ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያጸይፉ ናቸውና።
ከዚያ በኋላ የፈታት የመጀመሪያ ባሏ፥ የረከሰች በመሆኗ እንደገና መልሶ ሊያገባት አይችልም፤ ይህ በጌታ ፊት አስጸያፊ ነው። ጌታ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ኃጢአት አታምጣ።
የተቀረጸውንም የአምላኮቻቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላለህ፤ በእነርሱ ላይ የተለበጠውን ብር ወይም ወርቅ አትመኝ፥ በጌታ አምላካችሁም ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመድበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ።
ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበው የክርስቶስ ደም እንዴት ልቆ፥ ሕያው እግዚአብሔርን ለማምለክ፥ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን!