ዘዳግም 24:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ከዚያ በኋላ የፈታት የመጀመሪያ ባሏ፥ የረከሰች በመሆኗ እንደገና መልሶ ሊያገባት አይችልም፤ ይህ በጌታ ፊት አስጸያፊ ነው። ጌታ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ኃጢአት አታምጣ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ከዚያ በኋላ የፈታት የመጀመሪያ ባሏ፣ የረከሰች በመሆኗ እንደ ገና መልሶ ሊያገባት አይችልም፤ ይህ በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነው። አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ኀጢአት አታምጣ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 በሁለቱም መንገድ ቢሆን ያ የመጀመሪያ ባልዋ እንደገና ሊያገባት አይፈቀድለትም፤ እንደ ረከሰች አድርጎ ይቊጠራት፤ እርስዋን እንደገና ቢያገባ ይህ ድርጊት በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ ምድር ስትኖሩ እንደዚህ ያለውን አስከፊ ኃጢአት መፈጸም አይገባችሁም። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 የሰደዳት የቀድሞ ባልዋ ከረከሰች በኋላ ደግሞ ያገባት ዘንድ አይገባውም፤ ያ በእግዚአብሔር የተጠላ ነውና፤ አምላክህም እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሰጠህን ምድር አታርክስ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 የሰደዳት የቀድሞ ባልዋ ከረከሰች በኋላ ደግሞ ያገባት ዘንድ አይገባውም፤ ያ በእግዚአብሔር የተጠላ ነው፤ አምላክህም እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሰጠህን ምድር አታርክስ። Ver Capítulo |