የሰሎሞንም ግዛት ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ፍልስጥኤም ግዛት፥ ከዚያም አልፎ እስከ ግብጽ ወሰን ያለውን አገር ሁሉ ያጠቃልል ነበር፤ የእነዚህም አገሮች ሕዝቦች በጠቅላላ ሰሎሞን በነበረበት ዘመን ሁሉ ለእርሱ ተገዢዎች ሆነው ይገብሩለት ነበር።
ዘዳግም 15:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላክህ ጌታ በሰጠህ ተስፋ መሠረት ይባርክሃል፥ አንተም ለብዙ አሕዛብ ታበድራለህ ከማንም ግን አትበደርም፤ ብዙ አሕዛብን ትገዛለህ ማንም ግን አንተን አይገዛህም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት ስለሚባርክህ፣ አንተ ለብዙ አሕዛብ ታበድራለህ እንጂ ከማንም አትበደርም፤ ብዙ አሕዛብን ትገዛለህ እንጂ ማንም አንተን አይገዛህም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ይባርክሃል፤ አንተ ለብዙ ሕዝቦች ገንዘብ ታበድራለህ፤ ነገር ግን ከእነርሱ ከማንኛውም ሰው አትበደርም፤ አንተ በብዙ ሕዝቦች ላይ የበላይነት ይኖርሃል፤ በአንተ ላይ ግን ማንም የበላይ አይሆንም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ነገረህ ይባርክሃል፤ ለብዙ አሕዛብም ብዙ ታበድራለህ፤ አንተ ግን አትበደርም፤ ብዙ አሕዛብንም ትገዛለህ፤ አንተን ግን አይገዙህም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህም እግዚአብሔር ተስፋ እንደ ሰጠህ ይባርክሃል፤ ለብዙ አሕዛብ ታበድራለህ፥ አንተ ግን አትበደርም፤ ብዙ አሕዛብንም ትገዛለህ፥ አንተን ግን አይገዙህም። |
የሰሎሞንም ግዛት ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ፍልስጥኤም ግዛት፥ ከዚያም አልፎ እስከ ግብጽ ወሰን ያለውን አገር ሁሉ ያጠቃልል ነበር፤ የእነዚህም አገሮች ሕዝቦች በጠቅላላ ሰሎሞን በነበረበት ዘመን ሁሉ ለእርሱ ተገዢዎች ሆነው ይገብሩለት ነበር።
ሰሎሞን ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ ያለውን ምድር ሁሉ ከቲፍሳሕ ከተማ ጀምሮ እስከ ጋዛ ከተማ ድረስ ይገዛ ነበር፤ ይህም ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ የሚገኙትን ነገሥታትን ሁሉ ያጠቃልላል፤ ጐረቤቱ ከሆኑት አገሮችም ሁሉ ጋር በሰላም ይኖር ነበር።
ስለዚህ ለጠላቶቻቸው እጅ አሳልፈህ ሰጠሃቸው፥ አስጨነቁአቸውም፥ በመከራቸውም ጊዜ ወደ አንተ ጮኹ፥ ከሰማይም ሰማሃቸው፥ እንደ ምሕረትህም ብዛት ከጠላቶቻቸው እጅ ያዳኑአቸውን ታዳጊዎችን ሰጠሃቸው።
ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካምም አድርጉ፤ ይመለስልናልም ብላችሁ ምንም ተስፋ ሳታደርጉ አበድሩ፤ ዋጋችሁም ታላቅ ይሆናል፤ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለማያመሰግኑና ለክፉዎች ቸር ነውና።